Addis Zemen (Sep 11, 2026)
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለሚያመርተው ቤኒር እና ፕላይ ውድ ጣውላ ግብዓት የሚሆን የባህርዛፍ ግንድ ጫካው ከሚገኝበት ከደ/ብርሃን ወደ ደሴ በሚወስደው መንገድ ከሚገኘው ሎት 1፡– ጉዶበረት ቀበሌ ልዩ ስሙ ጀርባ ምድር ደን ሣይት በግምት 150 ቢያጆ እና ሎት 2፡– አባሞቴ ቀበሌ ልዩ ስሙ ቡራ ደን ሳይት በግምት 150 ቢያጆ የተቆረጠ ግንድ የሚያመላልሱ ገልባጭ መኪኖችን በዘርፉ የተሰማሩ ባለንብረቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ከሆነው ባለንብረት ጋር የኮንትራት ውል በመግባት ግንዱ ተጭኖ እስከሚያልቅ ድረስ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት፡–
1. በዘርፉ የተሰማራና የንግድ ስራ ፈቃዱን ያሳደሰ
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸው
3. የቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትና ሌሎች የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. ተጫራቾች ለሁለቱም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት1:- 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ እና ለሎት 2፡– 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ ለሁለቱም ሎቶች ለየብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው፡፡
6. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው::
7. በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፤ ካለም አንድ ሰረዝ በማድረግ ፊርማቸውን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፤
8. ድርጅቱ ከፍያ የሚፈፅመው በቢያጆ ስለሆነ ለመኪናው የሚያስፈልገውን ወጭ የነዳጅ እና ሌሎች ሁሉንም ወጭዎች የሚሸፍነው ባለመኪናው ይሆናል፡፡
9. ተጫራቾች ኦሪጅናል የጨረታ ሰነድ በጥንቃቄ በታሽገ ፖስታ በካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀናት የሚቆይ ስለሆነ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታውን ሰነድ ገቢ ማድረግ ይችላሉ፡፡
10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ በካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ ውስጥ በይፋ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ከመከፈት አይታገድም፡፡
11. የመክፈቻ ቀኑ የህዝብ በዓል ወይም እሁድ ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
12. አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የሚሆን ገንዘብ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብር ለሎት 1፡– 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ እና ለሎት 2፡ 100000.00/አንድ መቶ ሺህ ብር/ ለሁለቱም ሎቶች ለየብቻ ማስያዝ አለበት፣ ሆኖም ያሸነፈው ተጫራች አንዱን ሎት ብቻ ከሆነ የሚያስይዘውም የውል ማስከበሪያ የአንዱን ብቻ ይሆናል፡፡
13. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ከካምፓኒው ፋይናንስ ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
14. መ/ቤቱ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0910 368 437 ደውለው ይጠይቁ
የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር
ደብረ ብርሃን