Addis Zemen (Sep 11, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
በቂርቆስ ክ/ከተማ የጤና ጽ/ቤት እፎይታ ጤና ጣቢያ ግ/ንብ/አስ/የስራ ሂደት በ2019 ዓ.ም በጀት አመት ለጤና ጣቢያው አገልግሎት የሚውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የቫት ተመዝጋቢ እና የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
2. የጨረታ ሰነዱን ብር 250 (ሁለት መቶ ሃምሳ ብር) ብቻ በመክፈል በመግዛት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስር ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 ሰዓት ከ7፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት በጤና ጣቢያው አራተኛ ፎቅ ግዥ ከፍለው ቢሮ ቁጥር 408 መግዛት ትችላላችሁ፡፡
3. የሎት ዝርዝር
|
ተ.ቁ |
የእቃው ዝርዝር በሎት |
የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሲፒኦ ወይም ቅድመ ሁኔታ ባስቀመጠው የባንክ ዋስትና |
|
ሎት 1.6211 |
የደንብ ልብስ |
5000.00 |
|
ሎት 2. 6212 |
አላቂ የቢሮ እቃዎች |
5000.00 |
|
ሎት 3.6213 |
ህትመት |
5000.00 |
|
ሎት 4. 6218 |
ሌሎች አላቂ የፅዳት እቃዎች |
5000.00 |
|
ሎት 5.6219 |
ልዩ ልዩ መሳሪያዎች |
5000.00 |
|
ሎት 6. 6243 |
ለፕላንት ለማሽነሪ እና ለመሳሪያ እድሳትና ጥገና |
5000.00 |
|
ሎት 7. 6313 |
ለፕላንት ለማሽነሪና ለመሳሪያ መግዣ (ቋሚ እቃ) |
10,000.00 |
|
ሎት 8.6244 |
ለቁሳቁስ ህንፃ እና ለተገጣጣሚዎች እድሳት ጥገና |
10,000.00 |
|
ሎት 9.6221 |
ለህንፃ የግብርና እና የደንና የባህር ውስጥ ግብዓት |
5000.00 |
|
ሎት 10.6271 |
የአገር ውስጥ ስልጠና |
3000.00 |
|
ሎት 11.6214 |
አላቂና ቋሚ የህክምና እቃዎች |
5000.00 |
4. ማንኛውም ተጫራች መ/ቤቱ ናሙና ማቅረብ ይኖርበታል ባላቸው እቃዎች ላይ ናሙና ከጨረታው መክፈቻ እለት ከሁለት ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
5.ማንኛውም ተጫራች በኢንቨሎፕ በማሸግ በሁለት ፖስታ በማድረግ እላያቸው ላይ ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት መጻፍ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም ያቀረቡትን CPO በኦርጅናል ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል፡፡ጨረታው መዝጊያ እለት አስከ 11፡30 ሰአት ድረስ ጤና ጣቢያው ባዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ፡፡
6. ጨረታው ጋዜጣ ላይ ከወጣበት በ10ኛ ቀን 11፡30 ታሽጎ በሚቀጥለው የስራ ቀን በዓል ከሆነ ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእፎይታ ጤና ጣቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
7 አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱን አረጋግጦ ውል ከተዋዋለ በኋላ ያሸነፈበትን እቃዎች በተቋሙ ንብረት ክፍል ድረስ በ7 ቀን (ሰባት ቀን ውስጥ) የማቅረብ ሀላፊነት አለበት
8. ለሎት 8. የሚወዳደሩ ተወዳዳሪዎች ወቅታዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ እንደተጠበቀ ሆኖ ከደረጃ 6 እና ከዛ በላይ ማንኛውም ስራ ተቋራጭ ከፌደራል ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የምስክር ወረቀት ያላቸው እና ከአዲስ አበባ ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን ይጠበቅባቸዋል ::
9. የግንባታ ፈቃድ ያለው ሆነው የመልካም የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት ፡፡
10. ለጨረታ የሚቀርቡ እቃዎች ጥራታቸውን የጠበቁ መሆን አለባቸው፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ ፡– ጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራቶች አምራች መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማምጣት አለባቸው፣ በድጋፍ ደብዳቤ የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በቂ/ክ/ከተማ ጤ/ጽ/ቤት እፎይታ ጤና ጣቢያ የግ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ልዩ ቦታው ቦሌ ማተሚያ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ከዳንዲቦሩ ትምህርት ቤት ጀርባ ይገኛል፡፡
ስልክ ቁጥር 011 557 6523 / 011 557 417
በቂርቆስ ክ/ከተማ የጤና ጽ/ቤት እፎይታ ጤና ጣቢያ