የወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለግቢው ሠራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት የሚውሉ ከ 60ሰው በላይ የመጫን አቅም ያለው ተሽከርካሪ በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለግቢው ሠራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት የሚውሉ ከ 60ሰው በላይ የመጫን አቅም ያለው ተሽከርካሪ በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 13, 2026)

የጨረታ ማስታቂያ

የወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለግቢው ሠራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት የሚውሉ 60ሰው በላይ የመጫን አቅም ያለው ተሸከርካሪ በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ጨረታውን መሳተፍ የምትፈልጉ ሕጋዊ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በሆስፒታሉ በሚገኘው የግዥ ሥራ አስፈጻሚ በመቅረብ የተዘጋጀውን ሰነድ 200 ብር በመክፈል በመውስድ የመወዳደሪያ ዋጋችሁን በመሙላት

  1. የታደሰ መንጃ ፈቃድ፣ የቲን ሰርተፊኬት፣ በዘመኑ የቴክኒክ ምርመራ የተደረገበትን ቦሎና የባለቤትነት መታወቂያ ሊብሬ _ ኮፒ፣ ለዘመኑ የታደሰ የመድን ዋስትና እንዲሁም ለሶስተኛ ወገን አስገዳጅ የመድን ዋስትና የገቡበትን ሰነድ ኮፒ አያይዛችሁ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 (በአስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት 230 630 ሰዓት ከሰዓት 730-1130 ሰዓት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በግዥ ሥራ አስፈጻሚ ክፍል ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡
  3. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ዋጋ 15000 ብር /አስራ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረ CPO /ሲፒኦ/ የጨረታ ዋስትና ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ጨረታው 15ኛው ቀን 0800 ተዘግቶ 15 ቀን ከሰዓት በኃላ 830 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ የመክፈቻውም ቀንቅዳሜና እሁድ ወይም በሕዝባዊ በዓላት ላይ ከዋለ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  5. ሆስፒታሉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0913213696 ደውሉ መጠየቅ ይችላሉ

የወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *