የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ለ2019 ዓ.ም የምርት ዘመን ለስኳር ምርት ግብዓትነት የሚያገለግል ትኩስ ኖራ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ለ2019 ዓ.ም የምርት ዘመን ለስኳር ምርት ግብዓትነት የሚያገለግል ትኩስ ኖራ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 15, 2026)

ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር (LP/0T/02/SIG/2018/19

1. የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ለ2019 ዓ.ም የምርት ዘመን ለስኳር ምርት ግብዓትነት የሚያገለግል ትኩስ ኖራ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

2. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ህጋዊ ለ2018/19 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የምስክር ወረቀት/ የታክስ ክሊራንስ ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin No.) ሠርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ሌላ የሚመለከተው የመንግስት አካል ባዘጋጀው የዕቃ አቅራቢዎች አገልግሎት ሰጪ ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን/መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።

3. ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (ብር አምስት መቶ) በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጥር 1000000888862 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ ዘወትር – በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ፣ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡ 00፣ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-11፡00 ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ
ግዥና ንብረት አስተዳደር መምሪያ አድራሻ አዲስ አበባ ልደታ ክ/ከተማ ጨስስቅ አልሳም ህንጻ ፊት ስፊት
ፊሊፔስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 220
ስልክ ቁጥር +251 11 551 6271 ወይም 11 550 0417፣

4. ተጫራቾች የመጫረቻ አዲስ አበባ፣ኢትዮጵያ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተራ ቁጥር 3 በተገለፀው አድራሻ መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8፡15፤ ይከፈታል። ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተመሠከረለት የክፍያ ማዘዣ (CPO) ከቴክኒክ መጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ ለስልሳ (60) ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።

7. የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለሰላሳ (30) ቀናት ይሆናል።

8. ግሩፑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *