የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 16, 2026)

የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን ተሽከርካሪዎቹን ከቀን 07/01/2019 ጀምሮ ሳምፕል በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገልፃል፡፡

ማሳሰቢያ፦ ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et  ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፣

ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-

1. በተሽከርካሪ የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፤ ማንኛውም ተጫራቾች 100 ብር በመክፈል ከኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡

2. በሐራጅ ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) በተለያዩ ባንኮች በጉምሩከ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት ስም ሲ.ፒ.ኦ. በማሰራት ያሰሩትንም ሲ.ፒ.ኦ. በአካል ወደ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን ኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ፡፡

3. ለሀራጅ ጨረታ ቅ/ጽ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ያለው ከሆነ ከመነሻ ዋጋ ተነስቶ እንዲሁም መነሻ ዋጋ የሌለው ከሆነ ተጫራቹ የራሱን መነሻ በማስቀመጥ በኦንላይን በኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፤

4. ተጫራቹ በጨረታው አሸንፎ የገዛውን ተሽከርካሪ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ የሚረከብ መሆን አለበት፤

5. ተሸከርካሪውን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ለመንግስት ገቢ ይሆናል፤

6. በጨረታው ያላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፤

7. አሳማኝ የሆነ ምከንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል፤

8. ማንኛውም ተጫራች ተሽከርካሪውን ካሸነፈ በኋላ ከጅግጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈልግ እንደየ ቦታው ርቀት በቀነ ገደብ መሸኛ ሊሰጣቸው ይችላል፡፡

9. ተጫራቹ ተሽከርካሪውን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም፤

10. ለሀራጅ ጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 05 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በቀን 11/01/2019 ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡

11. የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር 09-05-11-55-11 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

NB: አሸናፊው ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) 15% (አስራ አምስት ፐርሰት) የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ፤ ተሽከርካሪዎቹን ሳያዩ የሚጫረቱ ተጫራቾች ቅ/ጽ/ ቤቱ ሆነ ኦክሽን ኢትዮጵያ ኢማ ሀላፊነቱን አይወስድም፡፡

 የሻንሲ እና የሞተር ቁጥር የተመታ ተሽከርካሪ ገዝተው መንገድ ትራንስፖርት ሰሌዳ ቁጥር ሲያወጡ መሸጥ እና መለወጥ የማይችሉ እና ቀይ ምልክት ያለው ሰሌዳ በመስጠት በመንገድ ትራንስፖርት በኩል መስተናገድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *