የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ጎልፍ ክለብ የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ጎልፍ ክለብ የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 20, 2026)

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ጎልፍ ክለብ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. ሸቀጣ ሸቀጥ የምግብ
  2. አትክልትና ፍራፍሬ
  3. ስጋና የስጋ ውጤቶች 
  4. የፅህፈት መሣሪያ
  5. የአሣና የአሣ ውጤቶች 
  6. ወተት
  7. የሰራተኞች አልባሳት

ስለሆነም ከዚህ በታች በተቀመጠው ዝርዝር መወዳደሪያ መስፈርቱን የምታሟሉ ህጋዊ ድርጅቶች በጨታው እንድትሣተፉ ይጋብዛል፡፡

1. ተጫራቾች የዘመኑ ግብር የከፈሉና በዘርፉ ህጋዊ የታደሠ ንግድ ፈቃድ ያለው ፣የንግድ ምዝገባ ሠርተፍኬት የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(ቲን ሰርተፍኬት) የገቢዎች የግብር ከፋይ ክሊራንስ ሰርተፍኬት (በአቅራቢነት የተመዘገቡ ንግድ ፍቃድ) ማረጋገጫ ማቅረብ አለበት፡፡

2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 10/1/2019 ጀምሮ ባሉት 15(አስራ አምስት) ቀን ውስጥ በመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ጎልፍ ክለብ ግዥ ክፍል በመቅረብ የማይመለስ ብር 700.00(ሰባት መቶ ብር) በመክፈል ሠነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00 ለያንዳዱ ሰነድ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒአ) ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት፡፡ 

4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ሰነድ ለየብቻ በታሸገ ፖስት ሆኖ በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ ህጋዊ ማህተም ማድረግ ጨረታውን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን 10/1/2019 ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በስራ ሰዓት ለዚህ በተዘጋጀው ጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለበት:

5. ጨረታው በ16ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ ከቀኑ 8፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ጎልፍ ክለብ ስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ጨረታው ይከፈታል፡፡

6. ዘግይተው የሚደርሱ ማንኛውንም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም::

7, የጨረታ አሸናፊዎች ማሸናፋቸውን በፅሑፍ የሚገለፅላቸውንና የውል ስምምነት የሚፈፅሙ ይሆናል፡፡

8 ህጋዊ መስፈርት የማያሟሉ ተጫራቾች ወዲያውኑ በእለቱ ከጨረታ ተወዳዳሪነት ውጪ ይሆናል።

9 መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ተጨማሪ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 011369-15-33 /0940248638
በመደወል ወይም
አድራሻ፡- ጦር ሀይሎች ሞቢል ፊት ለፊት ኡማ ሆቴል 100 ሜትር ገባ ብሎ በመቅረብ መረዳት ይቻላል፡፡
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ጎልፍ ክለብ