የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት 2019 በጀት ዓመት በወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የጽህፈት መሣሪያዎች፣ ጽዳት ዕቃዎች እና ባለሁለት እግር ተሽከርካሪዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት 2019 በጀት ዓመት በወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የጽህፈት መሣሪያዎች፣ ጽዳት ዕቃዎች እና ባለሁለት እግር ተሽከርካሪዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 25, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት 2019 በጀት ዓመት በወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ዕቃዎችን ከዚህ በታች

  • በሎት 1. የጽህፈት መሣሪያዎች
  • በሎት 2. ጽዳት ዕቃዎች
  • በሎት 3. ባለሁለት እግር ተሽከርካሪዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል እና የዘመኑን ግብር የከፈለ/ለች።

2. በዘርፉ የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል/የምትችል።

3. ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ እና ኮፒውን አያይዞ ማቅረብ የሚችል/ የምትችል።

4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ማቅረብ የሚችል/የምትችል።

5. የዘመኑን ግብር የከፈለ/ለች እና ክሊራንስ ከግብር መ/ቤት ያቀረበ።

6. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ የሚችል።

የሎት ቁጥር

የሎት ዝርዝር

የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና በኢትዮጵያ ብር

ምርመራ

 

ሎት 1

የጽህፈት መሣሪያዎች

50,000

 

ሎት 2

ጽዳት ዕቃዎች

20,000

 

ሎት 3

ባለሁለት እግር ተሽከርካሪዎች

50,000

 

7. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 /ሃያ አንድ/ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ21ኛው ቀን ከሰዓቱ 9፡00 ላይ ታሸጎ በዚያው ቀን ከቀኑ 9፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል። እለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

8. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በአሃዝ እና በፊደል መግለጽ አለባቸው። በፊደል እና በአሃዝ መካከል ልዩነት ካለው በፊደል የተገለጸው ይወሰዳል።

9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር ሶስት መቶ /300/ በመክፈል ከደ/ቤ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10/አስር/ በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ፋይናንሻል አንድ /1/ ኦርጅናል እና ሁለት /2/ ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል አንድ/1/ ኦርጅናል እና ሁለት /2/ ኮፒ ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

11. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ ወይም ያላካተተ መሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል። ያለበለዚያ ያቀረቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ ተደርጎ ይወሰዳል።

12. ተጫራቾች በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ ፊርማቸውን እና የድርጅታቸውን ማህተም ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

13. ተጫራቾች የጨረታ ፖስታውን የደ/ቤ/ወ/ፋ/ኢ/ኮ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

ማሳሰቢያ፡–መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡– የደ/ቤ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት

ደ/ወርቅ ስልክ ቁጥር፡– 0910997747/0917503586/0929241731 በመደወል መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ።

የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *