Addis Zemen (Sep 25, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
ሪዬስ ኢንጂነሪንግ አ.ማ. የእርሻ ማሽነሪ መለዋወጫ ዕቃዎች የፐርኪንስ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በጨረታ ሰነዱ ላይ ለተዘረዘሩት የተለያዩ የማሴ ፈርጉሰን እና የፐርኪንስ መለዋወጫ ዕቃዎች አጠቃለይ መመሪያዎች እና ግዴታዎች፡–
1. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ደንበኞች የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርበታል።
2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 11:00 ሰዓት ድረስ የሚጫረትበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማቅረብ በጨረታ ሰነድ ቅጽ ላይ በመሙላት ለጨረታ ማስከበሪያ የቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) CPO ብቻ በማስያዝ በሳሪስ ቶታል አቅራቢያ በሚገኘው የኩባንያው የእርሻ ማሽነሪ መለዋወጫ ዕቃዎች ንዑስ ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
3. በዚህ የግዥ ጨረታ የሚቀረቡ ሰነዶች በሙሉ በአማርኛ ወይም በእንግሊዝኛ ቋንቋ ብቻ መጻፍ ይኖርበታል።
4. ተጫራቾች ለመግዛት የወሰነበትን ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን ሳይጨምር ለእያንዳንዱ መለዋወጫ ዕቃ መለያ ቁጥር በተናጥል መጥቀስ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች የሚፈልጉትን የመለዋወጫ ዓይነት በማየት በጥቅል ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በሥም በታሸገ ኤንቨሎፐ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. የጨረታ ሰነዱን መግዣ የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) ለኩባንያው ገንዘብ ተቀባዮች ገቢ በማድረግ ከእርሻ መሳሪያዎች መለዋወጫ ንዑስ የሥራ ክፍል መውሰድ ይችላሉ።
7. ከተጠቀሰው ጊዜ በኋላ ዘግይተው የሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።
8. ጨረታ የጨረታ ሰነዱን መክፈቻ ጊዜ ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቸው በተገኙበት ትራንስ ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ በሚገኘው የኩባንያው የስልጠናና የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።
9. የጨረታ አሸናፊዎች ማሸነፋቸው በማስታወቂያ ከተገለጸ ቀን አንስቶ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ያሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ ተጨማሪ ዕሴት ታክስን ጨምሮ ክፍያ መፈጸም ይኖርባቸዋል።
10, በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ክፍያ ፈጽመው ያሸነፈበትን ዕቃዎች የማያነሱ ከሆነ በዕቃዎቹ ላይ ለሚደርሰው ጉዳት ኩባንያው ተጠያቂ አይሆንም።
11. የጨረታ ተሸናፊዎች ዝርዝር በማስታወቂያ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ለጨረታው ያስያዙትን CPO ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
12. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 011 442 1133 / 0911 560 658
ሪዩስ ኢንጂነሪንግ አ.ማ