Melekite Dire (Sep 23, 2026)
የአካባቢ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን ለ2019 በጀት ዓመት አላቂ የጽዳት እቃዎች እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን በአካባቢ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
|
Lot/ ምደብ |
የእቃው ዓይነት |
|
Lot 1 |
አላቂ የቢሮ ዕቃዎች |
|
Lot 2 |
አላቂ የጽዳት ዕቃዎች |
ስለዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ በዕቃና አገልግሎት አቅራቢነት በፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር መመዝገቡን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት መወዳደሪያ ኤንቨሎፑ ውስጥ በማድረግ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታው ዶክመንት የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር ብቻ / በመክፈል ድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን ከግዥ ፋይናንስና ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 9 በጥሬ ገንዘብ በመከፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ በውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን ቢሮ ቁጥር 09 ከ1፡30 እስከ 11፡30 ዘወትር በስራ ሰዓትና ቀን መግዛትና ማስገባት ይቻላል፡
- ጨረታው በማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን በ3፡30 የጨረታ ሳጥኑ ተዘግቶ በተመሣሣይ ቀን 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለሎት አንድ ብር 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር/ ለሎት ሁለት ብር 30,000.00(ሰላሳ ሺብር ብቻ) የጨረታ ማስከበሪያ በተረጋገጠ የባንክ ዋስትና CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ዶክመንቱ ሲከፈት ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታው ዶክመንት በታሸገ ፖስታ የእያንዳንዱ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ በግልጽ ማስቀመጥ አለበት በተጨማሪ በጨረታ ዶክመንቱ ውስጥ የተዘጋጁት ፎርማት ተሞልተውና ተፈርመው መቅረብ አለባቸው፡፡
- ያሸነፈው ተጫራች የተጠየቀውን እቃ የግዥ ትዕዛዝ እንደተሰጠው በእስፔስፊኬሽኑ እና በናሙናው መሠረት በ15 ቀናት ውስጥ በድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን በሚገኝበት መጋዘን አቅርቦ ማስረከብ አለበት፡፡
- በዶክመንቱ ከተሰጠው ስፔስፊኬሽን ወይም ሳምኘል ወጪ የሚቀርብ ተቀባይነት የለውም፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ካሸነፈው ዋጋ 10% ውል ማስከበሪያ በተረጋገጠ የባንክ ዋስትና CPO ወይም በሁኔታ ያልተገደበ የባንክ ጋራንቲ ማስያዝ መስጠት የሚችል መሆን አለበት ፡፡
- በጨረታው ሂደት ጨረታውን ለማዛባት ለማጭበርበር የሞከረ ተጫራች ከጨረታው ውጭ እንደሚሆንና በመንግሥት ግዢ እንዳይሳተፍ ይደረጋል፡፡
- ጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ዶክመንት ተባይነት የለውም፡፡
- ባለስልጣን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡– ድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን ቀበሌ 03
ድሬዳዋ
ስልክ ቁጥር 025 112 4892