በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የቡልጋ ከተማ አስተዳደር ለከተማ አገልግሎት የሚውል ፒካፕ ቲዮታ ሚኒ ጋቢና ተሽከርካሪ ለ2019 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የቡልጋ ከተማ አስተዳደር ለከተማ አገልግሎት የሚውል ፒካፕ ቲዮታ ሚኒ ጋቢና ተሽከርካሪ ለ2019 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 28, 2026)

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 03/19

በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የቡልጋ ከተማ አስተዳደር ለከተማ አገልግሎት የሚውል ፒካፕ ቲዮታ ሚኒ ጋቢና ተሽከርካሪ ለ2019 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፤

ስለዚህ ተጫራቾች –

1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው እና የታደሰ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው

3. ግዥው ለመሳተፍ የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክርነት ወረቀት እና የታክስ ክሪላንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

5. የሚገዙ እቃዎችን አይነት ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊክሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200/ ሁለት መቶ ብር ብቻ በመክፈል ከግዥና ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 ማግኘት ይችላሉ።

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድቦንድ ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ ለጽህፈት ለመኪና ኪራይ 10000/አስር ሽህ ብር ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይችላሉ።

8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ሞልተው በመፈራረምና የድርጅቱን ክብ ማህተም በማድረግ ዋናና ኮፒውን በመለየት 2ቱንም ፖስታዎች ማለትም ዋናና ኮፒውን የተጫራቹን ስምና አድራሻ በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ አየር ላይ ከወጣበት ተከታታይ ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን 3፡30 ድረስ ጽ/ቤቱ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቡ /ከ /አስ/ገንዘብ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:31 ታሽጎ በዛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል። 11ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል። የተሽከርካሪ አይነትና ሞዴል በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል።

10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11. በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ላይ ያልተገለፁ በጨረታ ሰነዱ ላይ በዝርዝር ይገለፃሉ።

12. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 011 673 9506 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

አድራሻ ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ብርሀን በሚወስደው መንገድ ከአዲስ አበባ 65 ኪ.ሜ ርቀት ከፍቼ ገነት ከተማ አለፍ ብሎ
የቡ/ከ/አስ/ገንዘብ / ጽ / ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *