የመኪና ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ – test3.diretenders.com

የመኪና ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


Addis Zemen (Sep 29, 2026)

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት እስክንድር ወ/ሰንበት እና በፍ/ባለዕዳ ትዕግስት እንዳለ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.136362 በ03/12/2014ዓ.ም እና የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.13413 በቀን 24/10/2017ዓ.ም በዋለው ችሎት በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 06 ሮሆቦት የመኪና ማቆሚያ ግቢ ውስጥ ቆሞ የሚገኘው የሰ/ቁ ኮድ 2- B52056አ.አ RAV4 ተሽከርካሪ የሐራጅ መነሻ 7,407,180 ( ሰባት ሚሊዮን አራት መቶ ሰባት ሺህ አንድ መቶ ሰማንያ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 9 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ5፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥሲሆን፣ ንብረቱንተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። 1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤጽ/ስም CPO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 11 273 0852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ / ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *