Addis Zemen (Sep 28, 2026)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 03/2019፣ 04/2019፣ 05/2019 እና 06/2019
ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን እየገነባቸው ላሉት
- ለተለያዩ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የሳኒተሪ እቃዎች አቅርቦት እና አቅርቦትና ገጠማ ጨረታ ቁጥር 03/2019
- ለከለላ ከተማ አስተዳደር ቢሮ ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ የአልሙኒየም በርና መስኮት እና PVD Coated golden mirror አቅርቦት እና ገጠማ ስራ ጨረታ ቁጥር 04/2019
- ለወግዲ ወረዳ አስተዳደር አዳራሽ ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ ስካይ ላይት፣ አልሙኒየም ሲሊንግ እና የአልሙኒየም በርና መስኮት አቅርቦት እና ገጠማ ስራ ጨረታ ቁጥር 05/2019
- ለደባርቅ ንግድና ገበያ ማዕከል ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ የአልሙኒየም በርና መስኮት አቅርቦት እና ገጠማ ስራ ጨረታ ቁጥር 06/2019 ግዥ ለመፈጻም ህጋዊና ብቃት ያላቸው ፋብሪካዎችና አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤
1. በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው/ያላት፤
2. የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል፣
3. የጨረታ ሰነዱን ባ/ዳር ከተማ ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ቀበሌ 11 እና አ/አበባ ለገሃር አመልድ ህንፃ በሚገኘው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ 7ኛ ፎቅ ለተጠቀሱት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት መውሰድ ይችላሉ።
4. የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀናት ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት በተለያዩ ፖስታዎች በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለጨረታ ቁጥር 03/2019፣ 04/2019፣ 05/2019 እና 06/2019 እስከ 15ኛው ቀን (15 ተከታታይ ቀናትን በመቁጠር) ባህር ዳር ዋናው ቢሮ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሣጥኑ ለጨረታ ቁጥር 03/2019፣ 04/2019፣ 05/2019 እና 06/2019 በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል። የተጠቀሱት የመክፈቻ እና የመዝጊያ ቀናቶች የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በእለቱ ቀን 8፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል።
5. የጨረታው ውድድሩ በሎት/በምድብ/ ድምር ዋጋ የሚታይ ሲሆን በአንድ ሎት ምድብ ለተጠየቁ የስራ ዝርዝሮች ሙሉ በሙሉ ዋጋ መሞላት አለበት።
6. በጨረታ የተሞላው ዋጋ የጨረታ ሠነዱ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ45 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ ይቆያል።
7. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር
ባህርዳር፡– 058-218-0538 / 09-18-01-06-17 / 09-18-16-43-93 / 09-12-00-21-87 / 09-21-25-89-20/ 09-21-26-13-00
አዲስ አበባ ፡– ስልክ ቁጥር 011 126 5338 / 09-18-80-03-64 / 09-11-90-86-29
የዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን