Addis Zemen (Sep 28, 2026)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአራዳ ክፍለ ከተማ ጃንሜዳ ጤና ጣቢያ በ2019 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ጨረታ ቁጥር 001/2019 ለጤና ጣቢያው አገልግሎት የሚውሉ ደንብ ልብስ፣ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፤ አላቂ የህክምና እቃዎች፣ ቋሚ የህክምና እቃዎች የጥገና፣ ህትመት ፤ የጥገና ዕቃዎች፣ የፈሳሽ ቆሻሻ ማንሳት የላውንደሪ ማሽን ጥገና፤ የጀኔሬተር ጥገና፤ የሚወገዱ መድሃኒቶች እና ልዩ ልዩ መሳሪያዎች በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት መጫረት የምትፈልጉ ተጫራቾች
1. በዘርፋ ህጋዊ ፍቃድ ያላችሁ
2. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገባችሁ
3. የታደሰ ህጋዊ ፍቃድ ወይም የዘመነን ግብር ከፋይ የሆናችሁ
4. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆናችሁ
5. ጨረታ ሰነድ ዋጋ ብር 300.00 ብር /ሶስት መቶ ብር ብቻ
6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ብር
|
ሎት |
የገንዘብ መጠን |
|
ሎት 1 የደንብ ልብስ |
13,000.00 |
|
ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች |
10,000.00 |
|
ህትመት |
9,000.00 |
|
ሎት 3 አላቂ የህክምና እቃዎች |
5,000.00 |
|
ሎት 4 የፅዳት እቃዎች |
2,000.00 |
|
ሎት 5 ቋሚ የቢሮ እቃዎች |
20,000.00 |
|
ሎት 6 የጥገና እቃዎች |
5,000.00 |
|
ሎት 7 የጀኔሬተር ጥገና |
10,000.00 |
|
ሎት 8 የላውንደሪ ማሽን ጥገና |
10,000.00 |
|
ሎት 9 የፈሳሽ ቆሻሻ ማንሳት |
10,000.00 |
|
ሎት 10 ቋሚ የህክምና እቃዎች ጥገና |
10,000.00 |
|
ሎት 11 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች |
2,000.00 |
|
ሎት 12 የሚወገዱ መድሃኒቶች |
5,000.00 |
በዚሁ መሰረት በጃንሜዳ ጤና ጣቢያ ስም በባንክ የተመሰከረለት CPO እና BID BOND ማስያዝ የሚችል ብቻ
7. ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ VAT 15% ያካተተ መሆን ይኖርበታል።
8. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ማቅረቢያ ጊዜ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ቀናት በጃንሜዳ ጤና ጣቢያ ውስጥ በፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 226 በመግዛት በታሸገ ፖስታ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በ11ኛው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን በተገኙበት የጨረታ ሰነዱ ይከፈታል።
9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10. ተጫራቾች ያሸነፋበትን እቃዎች ጃንሜዳ ጤና ጣቢያ ንብረት ክፍል ውስጥ ሙሉ ወጪውን ችለው ማስረከብ አለባቸው።
11. ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርበታል ማቅረብ ለማይችሉት በፎቶ ማቅረብ ይኖርበታል።
12. ፋይናሻል ኦርጅናል ፋይናሻል ኮፒ ማቅረብ ይኖርበታል።
13. ለበለጠ መረጃ ዝርዝር መረጃ ሰነድ ላይ መመልከት ይችላሉ።
አድራሻ ፡– ከ6 ኪሎ ወደ ጃንሜዳ የሚወስደው መንገድ ከቴሌው ፊት ለፊት አራዳ ክፍለ ከተማ ጃንሜዳ ጤና ጣቢያ ሲሆን
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 126 1509 / 011 126 1961 በመደወል መረጃ ማገኘት ይቻላል።
በአራዳ ክፍለ ከተማ የጃንሜዳ ጤና ጣቢያ