በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የየካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የየካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 28, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የየካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ሎት

የእቃው /የስራው ዓይነት

ከአጠቃላይ በጀት የተወሰደው መጠን በ%

ለየሎቱ የሚያስይዘው ማስከበሪያ /CPO/ መጠን

1

የደንብ ልብስ

0.5

9500.00

2

የደንብ ልብስ ስፌት

0.5

3500.00

3

አላቂ የቢሮና የጽዳት እቃዎች

0.5

5000.00

4

የጽህፈት መሳሪያ

0.5

5000.00

5

አላቂ ዕቃዎች

0.5

3500.00

6

ቋሚ እቃዎች

0.5

10000.00

7

የስፖርት እቃዎች

1

5000.00

8

የተለያዩ ጥገናዎች

1

5000.00

9

የቤተ ሙከራ እቃዎች

0.5

4500.00

በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል።

  • ተጫራቾች የንግድ ፍቃዳቸው Online የተመዘገበ መሆን አለበት።
  • በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈለ – ናሙና (ሳምፕል)ለሚፈለግባቸው ዕቃዎች ማቅረብ የሚችሉ
  • ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆነ ማስረጃ የሚያቀርብ – የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸው
  • በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ቢሮ ቁጥር 2 ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  • የጨረታው አሸናፊዎች ማሸነፋቸውን ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ 7/ሰባት/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ ባሸነፉባቸው ዕቃዎች ላይ _ 10%(ፐርሰንት) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝና ተዋውለው እቃዎቹን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው ዋጋ ማቅረቢያ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ(ቫት) ጨምሮ በመግለፅ ዋናውን እና ኮፒውን በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ ላይ በተጠቀሰው የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 2 ለዚህ ተብሎ ለተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  • በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ አካላት ሲሆኑ ሰነድ ለመውሰድ በሚመጡበት ወቅት ከሚመለከተው አካል ወቅቱን የጠበቀ በፅህፈት ቤቱ ስም የተፃፈ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም መወዳደር የሚችሉት በራሳቸው በተመረተ ምርት ብቻ ይሆናል።
  • ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2፡30-10፡00 ሰዓት ድረስ የካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በመገኘት የማይመለስ ብር 400.00/አራት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ
  • ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም”
  • ትምህርት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ለ10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛ ቀን በ3፡00/ሶስት/ ሰዓት ታሽጎ በ3፡30/ሶስት ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ/ ተጨራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  • ተጫራቾች የገዛችሁትን ሙሉ ሰነድ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር አብራችሁ ማስገባት አለባችሁ። ሙሉ ሰነዱን ያላስገባ ተጫራች ከውድድር ውጪ ይደረጋል።
  • የግዥ ውል በሚፈፀምበት ወቅት መ/ቤቱ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተመለከተው የዕቃ ብዛት እስከ 20 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 276 8120 / 011 230 3241 / 011 230 3054 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

አድራሻ፡– አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አውቶብስ ተራ ወደ መሳለሚያ በሚወስደው መንገድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮልፌ

የካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት