Be'kur (Sep 28, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የባ/ዳር ቅ/ጽ/ቤት የተለያዩ የምግብ እህሎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም መስፈርቶችን የሚያሟሉ ሁሉም ጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ።
1. ማንኛውንም ተጫራች የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉበትን መረጃና የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት)፣ ተመዝጋቢ ሠርተፊኬት፤ በዘርፉ የታደስ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ።
2. ማንኛውም ተጫራች የምግብ እህሉን በአካል በማየት የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) የጠቅላላ ዋጋውን 2 በመቶ ያላነሰ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
4. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው ጥቅምት 2/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ እለት ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 8፡30 ይከፈታል።
5. ተጫራቾች ጨረታ ሰነዱን በቅ/ፅ/ቤቱ ዘወትር በስራ ሰዓት በመገኘት መግዛት ይችላሉ።
6. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
7. አድራሻ ባ/ዳር ቀበሌ 16 ጉደር ዱቄት ፋብሪካ በስተጀርባ ሲሆን ለበለጠ መረጃ ለማግኘት በስልክ ቁጥር 09 78 74 49 59 /09 82 21 21 20 መደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ።
በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የባ/ዳር ቅ/ጽ/ቤት