Reporter (Sep 30, 2026)
የIFRS ኦዲት አገልግሎት ጨረታ ማስታወቂያ
የአራዳ አትክልት ተራ የገበያ ማዕከል አ.ማ በሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚያበቃው የሂሳብ ዓመት የIFRS የሕግ ኦዲት አገልግሎት ለመስራት በሞያው ብቁ የሆኑ እና ፍቃድ ያላቸውን ገለልተኛ የውጪ ኦዲተር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል::
ተጫራቾች የሚከተሉት መስፈርቶች አሟልተው መወዳደር ይችላሉ፤
1. የኢትዮጵያ አካውንታንቶች እና ኦዲተሮች ማህበር የሙያ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፤
2. ከሚመለከተው አካል የኢትዮጵያ የሂሳብ እና ኦዲት ቦርድ AABE 2018 ዓ.ም ኦዲት ፍቃድ ያለው፤
3. ከIFRS ጋር የተጣጣሙ የሂሳብ መግለጫዎችን ኦዲት በማድረግ ልምድ ያለው በተለይ በተመሳሳይ ቋማት ኦዲት ያደረገ፤
4. ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
5. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበ፤
ማሳሰቢያ
- ተጨራቾች ድርጅታችሁን ማንነት የሚገልፅ (Company Profile) ጋር የቴክኒካል ፕሮፓዛል አንድ ዋና እና ኮፒ እንዲሁም የፋይናንሻል ፕሮፓዛላቸውን አንድ ዋና እና ኮፒ አያይዘው በሰም በታሸገ ኤንቭሎፕ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የስራ ቀናት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::
- በIFRS ኦዲት አገልግሎቶች ጨረታ የተሳተፈ አክሲዮን ማህበሩ በዚህ ቀን ባወጣው በIFRS ትግበራ አገልግሎቶች ጨረታ መሳተፍ አይችሉም::
ጨረታው ጥቅምት 05 ቀን 2019 ዓ.ም ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ፕሮፓዛላቸው ተጨራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ 8፡00 ሰዓት በአ.ማ ቢሮ ይከፈታል::
አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0935 40 15 95/96 ማግኘት ይቻላል
አድራሻ፡– አዲስ አበባ ከተማ ክ/ከተማ አራዳ ወረዳ 1 የቤ.ቁ አዲስ ፒያሳ አትክልት ተራ ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር ጂ4-024