Addis Zemen (Oct 01, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን የጨንቻ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎችን ለሴክተር መ/ቤቶች አላቂ የጽ/መሣሪያዎችን የጽዳት እቃዎችንና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ነጋዴዎች መወዳደር ይችላሉ፡፡
1/ በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈላችሁ፡፡
2/ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው/ያላት)፤
3/ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN NO) ያለው(ያላት)፤
4/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለዉ(ያላት) ፣
5/ የዕቃ አቅራቢነት ምስክር ወረቀት ያለው(ያላት)፣
6/ ቫት በዋጋ ማቅረቢያ ላይ ካልተገለጸ እንደተገለጸ ተደርጎ ይወሰዳል፤
7/ አሸናፊ ድርጅቱ ያሸነፋቸውን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርትና ወጪ ወደ ጨንቻ ከተማ አስ/ር ፋ/ጽ/ቤት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
8/ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶችን ይህ ማስታወቅያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 በተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ከጨንቻ ከተማ አስ/ር ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 ቀርበው የማይመልስ 200 (ሁለት መቶ ብር) እያንዳንዱ ሰነድ በመክፍል መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
5/ ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ/ ብር 20,000(ሃያ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋዝ CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር በማያያዝ ይዞ መቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ አንቀበልም፡፡
10/ የጨረታ ማስከብሪያ ዋስትና ፀንቶ የሚቆየው በጨረታ ያሸነፉትን ዕቃ ሙሉ በሙሉ እስኪያቀርቡ ድረስ ነው
11/ ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 5፡30 የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በዕለቱ በ8፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
12/ በጨረታ ሰነድ ላይ የተገለጸው ዋጋ ከውል ጊዜ ጀምሮ ለ60 ቀናት የፀና ይሆናል፡፡
13/ ተጫራቾች ሁሉንም ሰነዶቻቸውን ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ በማድረግ በታሸገ ፖስታ የጨረታ ዋጋ ማቅርቢያ ሰነድ ዝርዝር ሙሉ በሙሉ በመሙላት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
14/ አሸናፊ ድርጅቱ ውል ሲገባ ውል ማስከበሪያ 10% (CPO) ማስያዝ አለበት አለበለዚያ በውሉ መሰረት ቅድመ ክፍያ ሳይቀበል ዕቃውን ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
ማሳሰቢያ፦ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ሞባይል ስልክ ቁጥር፡- 09 16 881 031 ይደውሉ:: በደቡብ ኢትዮጲያ ክልል በጋሞ ዞን የጨንቻ ከተማ አስ/ር ፋ/ጽ/ቤት ከአርባ ምንጭ 37 ኪ.ሜ ርቅት ላይ ትገኛለች።
በደ/ኢ/ክ/መ/ በጋሞ ዞን የጨንቻ ከተማ አስ/ር ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት