የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከ2018 በጀት ዓመት ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሶስት አመታት የማህበሩን ሂሳብ በውጭ አዲተር ማስመርመር ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከ2018 በጀት ዓመት ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሶስት አመታት የማህበሩን ሂሳብ በውጭ አዲተር ማስመርመር ይፈልጋል


Addis Zemen (Oct 02, 2026)

የኦዲት ሥራ ጨረታ ማስታወቂያ

በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በምዝገባ ሰርተፍኬት ቁጥር 7470 ተመዝግቦ የሚንቀሳቀሰው ሀገር በቀል ድርጅታችን ሴንተር ፎር ኢንክሉሲቭ ኤንድ ሰስቴነብል ፋይናንስ ከ2018 በጀት ዓመት ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሶስት አመታት የማህበሩን ሂሳብ በውጭ አዲተር ማስመርመር ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት

1. በኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ የተመዘገበና ሂሳብ ለማድረግ ብቃት ያለው፤

2. የምዝገባ እና የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤

3. የግብር መለያ ቁጥር

4. የወቅቱን ግብር የከፈለ እና

5. የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን ኦዲት ያደረገበትን የስራ ልምድ ማስረጃ የሚያቀርብ ፣

ከዚህ በላይ የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉና አስፈላጊውን የሰነድ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ የኦዲት ድርጅቶችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡ ስለሆነም መስፈርቱን አሟልተው በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አምስት (5) የስራ ቀናት የመወዳደሪያ ቴክኒካል ሰነዳቸውን ብቻ (PDF)ከዚህ በታች በተቀመጠው የኢሜይል አድራሻ መላክ የሚችሉ መሆኑን እናስታውቃለን።

ኢሜይል፡- info@cisfe.org  ወይም ibrahimbushera20@gmail.com 

ስልክ ቁጥር፡ 0913765855
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *