የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የጭነት መኪኖችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የጭነት መኪኖችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል


Reporter (Oct 04, 2026)

የሐራጅ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 1147/11 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል::

ተ.ቁ

የተበዳሪው ስም

የንብረቱ ባለቤት

የንብረቱ ስም እና ዓይነት

ሞዴል፣ ሞተር እና ሻንሲ ቁጥር

የሰሌዳ ቁጥር

የሐራጅ መነሻ ዋጋ (ብር)

ሐራጁ የሚከናወንበት ቀን እና ስዓት

1

ሸሙ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

ተበዳሪው

የጭነት

HFJ1020AE3፣ DA465Q-1001452-3HD9፣ LKHNF1BG0CAF01721

አአ-03-A34140

488,320.00

09/02/2019 3፡00 – 4፡00 ጠዋት

2

ሸሙ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

ተበዳሪው

የጭነት

HFJ1020AE3፣ DA465Q-1001240-3HD9፣ LKHNF1BGXCAF01676

አአ-03-A34329

488,320.00

09/02/2019 4፡00 – 5፡00 ጠዋት

በመሆኑም፡–

1. ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) በማስያዝ መጫረት ይችላል:: የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲፒኦ ማቅረብ ተመራጭ ነው::

2. ሐራጁ የሚከናወነው አምባሳደር አካባቢ በሚገኘው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ዋናው መስሪያ ቤት 42ኛ (ወለል) ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4203 ውስጥ ነው።

3. የንግድ ማህበርን ወክሎ ለመጫረት የማህበሩን መመስረቻ እና መተዳደርያ ደንብ የያዘና በማህበሩ ስም ንብረት ለመግዛት ስልጣን ያለው መሆን ያለበት ሲሆን ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ በማቅረብ ይሆናል::

4. ከመኖሪያ ቤት ውጪ ለጨረታ የቀረቡ ንብረቶችን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ሰዉ በሽያጩ ገንዘብ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፍላል::

5. የጨረታ አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል::

6. ንብረቶቹን ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋ/መስሪያ ቤት 42 ፎቅ በአካል በመቅረብ ባንኩ በሚያመቻቸው ፕሮግራም መሰረት መጎብኘት ይቻላል፡

7.በጨረታው ከፍተኛ የሆነ የጨረታ ዋጋ የሰጠ ተጫራች በባንኩ የጨረታ አሸናፊነት ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ ቀሪ የሽያጩን ገንዘብ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ያለበት ሲሆን ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ለሐራጁ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል::

8. ንብረቶቹን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ግለሰብ/ድርጅት የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ባጠናቀቀ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መረከብ ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም:: ገዢው በተጠቀሰው ጊዜ ንብረቶቹን ካልተረከበ ከንብረቶቹ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ወጪ ኃላፊነቱን ይወስዳል።

9.ባንኩ ሐራጁን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111-13-05-08 በመደወል ወይም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ዋና መ/ቤት 42ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ሕግ ክፍል በአካል ቀርቦ ማነጋገር ይቻላል::

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *