Addis Zemen (Oct 18, 2026)
የአንደኛ ዙር ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ የግዥ መለያ ቁጥር 001/2019
በን/ስ/ላ/ክ/ከ የወረዳ 02 ጤና ጣቢያ የ2019 ዓ.ም በጀት አመት የሚፈልጋቸውን፡
- ሎት 1 ደንብ ልበስ 10,000.00
- ሎት 2 አላቂ የፅዳት እቃዎች 10,000.00
- ሎት 3 አላቂ የቢሮ እቃዎች -12,000.00
- ሎት4 ቋሚ እቃዎች 16,000.00
- ሎት 5 መድሃኒት እና የላብራቶሪ ሪኤጀንት 30,500.00
- ሎት 6 የጥገና እቃዎች 5,000.00
- ሎት7 ትራንስፖርት – 2,000.00
- ሎት 8 ህትመት -5,500.00
- ሎት 9 የባዮ ሜዲካል የጥገና መሳሪያዎች 5,000.00
ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
በዚህ መሰረት ፡-
- በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው, ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ በመንግስት ግዥ ን/አስ/ኤጀንሲ ድህረ ገጽ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ የተመዘገቡ ፤ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታው ለእያንዳንዱ ሎት ለሚወዳደሩበት ሲፒኦ በባንክ የተረጋገጠ ከላይ በሎት የተሰጡትን ማስከበሪያ ብር ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን በጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በተከተታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በየሎቱ በመክፈል በን/ስ/ላ/ክ/ከ የወረዳ 02 ጤና ጣቢያ ጀሞ ሚካኤል (አፍሪካ ህንፃ) ፊት ለፊት በሚገኘው ቢሮ ቁጥር 50 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በፋይናንስ ግዥ ቢሮ ቁጥር 50 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጠን ውስጥ ማስገበት ይኖርባቸዋል፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ10ኛው ቀን (በአስረኛው ቀን) 11፡30 /አስራ አንድ ተኩል ይታሽጋል፤ በ11ኛው ቀን በቢሮ ቁጥር 50 አራት ሰዓት(4፡00) ይከፈታል፤ የመክፈቻው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጠለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ሎት ናሙና ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለሌሎች በቀረበው የፍላጎት መግለጫ መሰረት ማዘጋጀትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ከቫት ጋር ያለውን ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል ፤
- የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባየነት የለውም፤ ተጫራቾች 10% የውል ማሰከበርያ በማስያዝ ውል ይፈጽማል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚ መ/ቤቱ ድርስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ
አድራሻ ፡- በን/ ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 2 ጤና ጣቢያ ጣቢያ ጀሞ ሚካኤል (አፍሪካ ህንፃ ) ፊት ለፊት ይገኛል፡፡ ስልክ ቁጥር 0972 70 51 52
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ