Addis Zemen (Oct 20, 2026)
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በአፈ/ከሳሽ አቶ ጥላሁን ቀማቸው እና በአፈ/ተከሳሽ አቶ ሙሉነህ ለንሳሞ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ በሲዳማ ብ/ክ/መ/ማዕከላዊ ሲ/ዞ/ዳሌ ወረዳ ወንቴ ቀበሌ ውስጥ በአፈ ተከሳሸ አቶ ሙሉነህ ለንሳሞ ስም የተመዘገበ የነዳጅ ማደያ ላይ የሲዳማ ብ/ክ/መ/ ማዕከላዊ ሲ/ዞ/ዳሌ ወረዳ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ቅ/ጽ/ቤት አውጥተው በላኩት ዋጋ ግምት ብር 14,302,582.37 (አስራ አራት ሚሊየን ሦስት መቶ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ሰማኒያ ሁለት ብር ከ37/100ሣንቲም ) መነሻ ዋጋ በሐራጅ እንዲሸጥ እና የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ ከ09/02/2019ዓ/ም ጀምሮ እስከ ከ09/03/2019ዓ/ም ለ30 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ የሀራጅ ሽያጩ በ10/03/2019ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በግልጽ በሐራጅ እንዲሸጥ ተወስኗል።
ስለሆነም፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎች ለጨረታው ማስከበሪያ የመነሻ ዋጋውን 1/4ኛ በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ተኛ ፎቅ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሒደት ቢሮ – ቁጥር 030 በአካል ቀርባችሁ በማስያዝ እና ያስያዛችሁበትን ሕጋዊ ደረሰኝ ይዛችሁ በመቅረብ ጨረታውን መሳተፍ ትችላላችሁ።
- በጨረታው ለተሸነፈ ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስለታል ።
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ያሸነፈበትን የጨረታ ገንዘብ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል።
- ያሸነፈበትን የጨረታ ገንዘብ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ ካላደረገ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ሆኖ በድጋሚ ማስታወቂያ ወጥቶ ጨረታ ይካሔድበታል።
- ጨረታውን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የስም ዝውውር በፍ/ቤቱ ትእዛዝ ይፈፀምለታል።
- የጨረታው ሒደት የሚካሔደው 10/03/2019 ዓ/ም 4፡00-6፡00 ሰዓት በሲዳማ ብ/ክ/መ/ማዕከላዊ ሲ/ዞዳሌ ወራዳ ወንቴ ቀበሌ ውስጥ በአፈ/ተከሳሽ አቶ ሙሉነህ ለንሳሞ ስም የተመዘገበ የነዳጅ ማደያ ያለበት እንደሆነ አውቀው በተባለው ጊዜ እንድትገኙ ፍ/ቤቱ አዟል።
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት
ስር የሀዋሣ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት