Addis Zemen (Oct 21, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ውስጥ የጥገና የማስዋብ ስራና ኢንተሪየር ዲዛይን አጫርተን ማሰራት ስለምንፈልግ፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ቢሮ የሚገኝበት ቦታ በመገኘት ምልከታ በማድረግ መጫረት ይችላል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መጫረት ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች
- በዘርፉ ህጋዊ እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፡
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ ለመሆናቸው የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
- የግብር መለያ ቁጥር ወይም ቲን ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር 5,000.00 ወይም የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ % በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በጥሬ ገንዘብ ግዥ ፋ/ንብ/አስ/ዳይሬክተር ክፍል ቢሮ ቁጥር 1 ወይም በቢሮአችን የገቢ አካውንት በባንክ ማግኘት ይቻላል፣
- ግምገማ የሚያካሄደው በሁለት ደረጃዎች ሲሆን በመጀመሪያ ደረጃ ቴከኒካል ፕሮፖዛል ይገመገማል፤ ግምገማ ውጤቱ ከ70% በላይ ያመጡ ተጫራቾች የፋይናንሻል ፕሮፓዛል ይታያል፡፡ የሚሰጠው ነጥብም ቴክኒካል 70% ሲሆን ፋይናንንሻል ደግሞ 30% ነው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአፋር ብ/ክ/መን ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በግዥ ፋ/ንብ/አስ/ዳይሬከተር ወይም በቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 10 ቀን 2019 ዓ.ም. 2:00 ሠዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ ግዥ ፋ/ንብ/አስ/ዳይሬሮክተር ክፍል በቢሮ ቁጥር 1 በ 11ቀን በ 2019 ዓ.ም. በ 9:00 ሠዓት ይከፈታል፣
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 1 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር0033–6660617 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 033-3660020 short No 08697 በመደወል ማግኘት ይችላሉ ።
- አድራሻችን ሰመራ የተባበሩት ማድያ 200ሜትር ገባ ብሎ የሚገኝ ህንፃ ግራውንድ ቢሮ ቁጥር 1 ነው፡፡
በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ