Addis Zemen (Oct 25, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ ጨረታ መለያ ቁጥር 00/2019 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤ/ጽ/ቤት ወረዳ 03 የመሪ ጤና ጣቢያ የ2019 ዓ/ም የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ከዚህ በታች ለተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።
- ሎት 1 የደንብ ልብስና ስፌት፣
- ሎት 2 አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣
- ሎት 3 የጽዳት ዕቃዎች ፣
- ሎት 4 የህትመት ስራዎች
- ሎት 5 አላቂ የህክምና ዕቃዎች፣
- ሎት 6 ልዩ ልዩ ዕቃዎች፣
- ሎት 7 የጥገና እቃዎች &
- ሎት 8 ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ የላብራቶሪ ማሽኖች ሰርቪስ፣ የጀነሬተር ሰርቪስ እና የጭነት መኪና አገልግሎት መ/ቤቱ ባወጣው ስፔስፍኬሽን መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሕጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።
በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች፡–
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት የተመዘገበ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
3. የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፣
4. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
5. በማንኛውም ግልጽ ጨረታ ላይ ያልታገዱ መሆን አለበት።
6. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ C.PO. ብቻ ማቅረብ አለባቸው።
ሎት ቁጥር የሎት ዝርዝር የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ
- ሎት ı. የደንብ ልብስና ስፌት ብር 36,000.00
- ሎት 2. አላቂ የጽህፈት መሣሪያዎች ብር 38,000.00
- ሎት 3. የጽዳት ዕቃዎች ብር 17,000.00
- ሎት 4. የሕትመት ሥራዎች ብር 34,000.00
- ሎት 5. አላቂ የሕክምና ዕቃዎች ብር 239,452.00
- ሎት 6. ልዩ ልዩ ዕቃዎች ብር 18,000.00
- ሎት 7. የጥገና ዕቃዎች ብር 10,000.00
- ሎት 8. ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች ብር 240,000.00
- ሎት 9. የላብራቶሪ ማሽኖች ሰርቪስ፣ የጀነሬተር ሰርቪስ ብር 20,000.00
- ሎት 10 የጭነት መኪና አገልግሎት ብር 2,000.00
7. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር / በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 51 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ።
8. ተጫራቾች ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 /አስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በመሪ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 52 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥማስገባት አለባቸው።
9. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ታሽጎ በዚሁ ሰዓት 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እና በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይምህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
10. ተጫራቾች ላሸነፉባቸው ጠቅላላ ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው።
11. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ናሙና የማይቀርብባቸው ቋሚ ዕቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው በተጨማሪም በፎቶ በማንዋል አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
12. በጨረታ አሸናፊ ሆኖ የተመረጠ ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት ወረዳ 03 መሪ ጤና ጣቢያ ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
13. መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡–እያንዳንዱ ዋጋ ሲሞላ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት ዘግይቶ የመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
አድራሻ፡– ለሚ ኩራ/ክ/ከ/ወረዳ 03 መሪ ጤና ጣቢያ አያት አደባባይ አለፍ ብሎ ወደ አራብሳ በሚወስደው አስፓልት ዞን 5ት መንገድ 12 በኮሮኮንች መግቢያ መንገድ 1500 ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል።
ስልክ ቁጥር፡– 09 10 51 38 85
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤ/ጽ/ቤት ወረዳ 03 የመሪ ጤና ጣቢያ