ኢትዮ ጥራት ቻሪቲ ኦርጋናይዜሽን የ2018 በጀት ዓመት የሂሳብ አፈጻጸም ሪፖርትን እና የሂሳብ ሰነዶችን ኦዲት ለማስደረግ ብቃትና ሕጋዊ ፈቃድ ካላቸው የኦዲት አገልግሎት ሰጪዎች በግልጽ ጨረታ የዋጋና የቴክኒክ ብቃት ውድድር አድርጎ ማሰራት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ኢትዮ ጥራት ቻሪቲ ኦርጋናይዜሽን የ2018 በጀት ዓመት የሂሳብ አፈጻጸም ሪፖርትን እና የሂሳብ ሰነዶችን ኦዲት ለማስደረግ ብቃትና ሕጋዊ ፈቃድ ካላቸው የኦዲት አገልግሎት ሰጪዎች በግልጽ ጨረታ የዋጋና የቴክኒክ ብቃት ውድድር አድርጎ ማሰራት ይፈልጋል


Addis Zemen (Oct 25, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

ኢትዮ ጥራት ቻሪቲ ኦርጋናይዜሽን የ2018 በጀት ዓመት የሂሳብ አፈጻጸም ሪፖርትን እና የሂሳብ ሰነዶችን አዲት ለማስደረግ ብቃትና ሕጋዊ ፈቃድ ካላቸው የኦዲት አገልግሎት ሰጪዎች በግልጽ ጨረታ የዋጋና የቴክኒክ ብቃት ውድድር አድርጎ ማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም በዘርፉ ተገቢው ሕጋዊ ፈቃድ፣ ሙያዊ ብቃትና ልምድ ያላቸው የኦዲት አገልግሎት ሰጪዎች የጨረታ ሰነዳቸውን በማቅረብ እንዲወዳደሩ ጥሪ ያቀርባል።

ተ.ቁ

የግዥ ዓይነት

የጨረታ መለያ ቁጥር

ምድብ /ሎት

 

የጨረታ ማስከበሪያ ዋሰትና ብር መጠን

ጨረታው የሚዘጋበት ቀንና ሰዓት

ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት

1

የግዥው ዓይነት፣ የኦዲት አገልግሎት ግዥ (የ2018 በጀት ዓመት የሂሳብ አፈጻጸም ሪፖርትና የሂሳብ ሰነዶች ኦዲት) በግልጽ ጨረታ የቴክኒክ ብቃትና የዋጋ ውድድር።

ETCO/01/2019

 

01/2019

10000

 

ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ በተከታታይ የሚቆጠር ቀን ሆኖ በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት

በጋዜጣ ከወጣበት ቀን እንስቶ በተከታታይ የሚቆጠር ቀን ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት

በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ ተጫራቾች የሚክተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፤

1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ጠናቀው ስለመከፈላቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው።

2. በጨረታ ለመሳተፍ የሚችሉ መሆኑን ከኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የድጋፍ ደብዳቤ የሚያቀርቡ።

3. የግብር ከፋይ መለያ(TIN)ያላቸው፣

4. የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በኢትዮ ጥሪት ቻሪቲ ኦርጋናይዜሽን ስም CPO ወይም በባንክ ዋስትና የተረጋገጠ ተዘጋጅቶ መቅረብ አለበት።

6. ከላይ የተገለጸውን መስፈርት አሟልተው በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመከፈል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከላይ በሰንጠረዥ ከተጠቀሰው የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት በስራ ሰዓት ከድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 01 ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

7. ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1 እስከ 10 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ከቴክኒክ መወዳደሪያ ሰነድ ጋር አያይዘው በቴከኒክ ኢንቨሎፖች ውስጥ ማቅረብ አለባቸው።

8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ቴክኒካል ዋናና ኮፒ እና የፋይናንሻል ማስረጃዎችን ዋናና ኮፒ በመለየትዋና እና ኮፒ በአንድ ፖስታ ካኪ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ከላይ በሰንጠረዥ ከተጠቀሰው የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት በቢሮ ቁጥር 01 ለዚህ ለተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ተጫራቾች በጨረታ ሰነዳቸው ላይ እና በፖስታው ላይ የድርጅቱን ማህተም ፊርማ ማድረግ አለባቸው

9. ዘግይተው የደረሱ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፤ መ/ቤቱ የተሻለ ምንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አሲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፣ ገላን ኮንደሚኒየም፣ ሴንትራል ሕንፃ ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁ 09 99 08 75 35 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ ።

በኢትዮ ጥሪት የበጎ አድራጎት ድርጅት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *