የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጀር ግዥ እና ገጠማ ( Procurement of Supply, Installation Configuration & Testing of EV charger) አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጀር ግዥ እና ገጠማ ( Procurement of Supply, Installation Configuration & Testing of EV charger) አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Reporter (Oct 25, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

ERC DSPA ግ.ጨ.ቁ05/2019

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች የተጠቀሱትን አቅርቦቶች ፍላጎት ካላቸው የአገር ውስጥ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

1. የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጀር ግዥ እና ገጠማ ( Procurement of Supply, Installation Configuration & Testing of EV charger)

በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የሚከተሉትን ህጋዊ ሰነዶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡

    • የታደሰ ንግድ ፍቃድ
    • የተጨማሪ እሴት ታክስ
    • በዘርፉ የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት
    • የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት /ቲን/
    • ታክስ ክሊራንስ
    • ተጫራቾች በሽርክና በጥምረት በጋራ ወይም በቅንጅት የሚጫረቱ ከሆነ የመመስረቻ ሰነድ ማቅረብ አለባቸው
  • ርክክቡ የሚፈጸምበት ቦታ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋናው መስሪያ ቤት ነው
  • ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ለ 30 (ሰላሳ) ቀናት
  • የጨረታ ማስከበሪያ መጠን 75,000.00 (ሰባ አምስት ሺ ብር ) ሆኖ የጨረታ ማስከበሪያው
  • በሲ.ፒ.ኦ  ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ሆኖ ጨረታ ከተከፈተበት 60 (ስልሳ) ቀናት የሚቆይ መሆን ይኖርበታል
  • ሰነድ ለመግዛት የምትፈልጉ ተጫራቾች ሰነዱ በሚገኝበት የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና መ/ቤት በፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 32 የማይመለስ 1000/አንድ ሺ ብር/ በመክፈል መውሰድ ትችላላችሁ።
  • ጨረታው አየር ላይ የሚውልበት ቀን 15/02/2019 ዓ.ም
  • ጨረታው የሚዘጋው፡–30/02/2019 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ሆኖ በእለቱ ከሰዓት 9፡30
  • ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በጨረታው አከፋፈት ላይ መገኘት የሚችሉ መሆኑ፤
  • የሚቀርበው እቃ አይነትና ይዘት በጨረታ ሰነዱ የተገለጹ መስፈርቶችን አሟልቶ መቅረብ የሚችል
  • ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
  • ለበለጠ መረጃ እና ማብራሪያ ዋናው መስሪያ ቤት በሚገኝበት አዲስ አበባ መሻለኪያ ከሸዋ ዳቦ ፊት ለፊት የቀድሞው አራተኛ ክፍለ ጦር ግቢ በአካል ወይም በስልክ 011 470 2063/ 011 470 2064 መጠየቅ ይቻላል።

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን አዲስ አበባ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *