Reporter (Oct 25, 2026)
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር፡ Medx/TND/2018-003
የፕሮጀክቱ ስም፡ የመድኃኒቶች፣ የህክምና መሳሪያዎች ሪኤጀንት እና ማሽኖች የማጓጓዣ/ የትራንስፖርት አገልግሎት ዓመታዊ ግዥ
ሜዴክስ ዲያግኖስቲክስ ለ2019 በጀት ዓመት መድኃኒቶችን እና የህክምና መሳሪያዎችን ከአዲስ አበባ ድርጅቱ ባሉት ቅርንጫፎች ደሴ፣ ጎንደር እና ባህርዳር የትራንስፖርት/ማጓጓዣ አገልግሎት ለማግኘት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር እንዲችሉ ይጋብዛል።
- የዘመኑ ግብር የከፈሉ (tax clearance) እና የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(tin number) ያላቸው
- መድኋኒት እና የሕክምና ላቦራቶሪ ግብዐቶች ለማጓጓዝ የኢትዮጵያ ምግብና መድኋኒት አስተዳደር ባለስልጣን (EFDA) በሚፈቅደው እስታንዳርድ መሰረት የቅዝቃዜ መጠን ከ8-15 ዲግሪ ሴንቲግሬድ የሆነ ቫን መኪና ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
- ለሚያጓጉዙት ግብዓት ለሚደርስ ማናቸውም ጉዳት አሸናፊው ድርጅት የጉዳቱን መጠን የኢንሹራንስ ሽፋን ይሰጣል።
- ሜዴክስ ለሚገዛቸው መድሃኒቶች እና ግብዓቶች ከፋብሪካ፣ ከአቅራቢ ድርጅቶች ወዘተ… በመሄድ ለመረከብ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት የሚችል መሆን አለበት።
- የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጠው ድርጅት በአዲስ አበባ ጊዜያው እስቶር ያለው እና መድኃኒቶች በጊዜያዊነት የሚከማቹበትን ሁኔታ ማመቻቸት አለበት።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል ሜዴክስ ዲያግኖስቲክስ ፋይናንስ ክፍል በመቅረብ ማግኘት ይችላሉ።
- አሸናፊው ድርጅት የሚመረጠው በተናጠል ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ድርጅት ሲሆን እንደ አስፈላጊነቱ እና አዋጭነቱ በሜዴክስ በኩል ተመዝኖ ለአንድ ተጨማሪ በጀት ዓመት ውሉ ሊራዘም ይችላል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ሜዴክስ ዲያግኖስቲክስ ግቢ ውሥጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ የጨረታ ማስታዎቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የቴክኒካልና ፋይናንሻል ምላሻቸውን በተለያየ ፖስታ አሽገው ማቅረብ ሲኖርባቸው የጨረታ ማስከበሪያ CPO 50,000.00 ብር (ሃምሳ ሺህ ብር) ከፋይናንሻል የዋጋ ማቅረቢያው ጋር አብሮ ይታሸጋል።
- ጨረታው በቀን 07/03/2019 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ይታሸግና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቀጣይ ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ሬስ ኢንጅነሪንግ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ሜዴክስ ዲያግኖስቲክስ ፋይናንስ ክፍል በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 6668 / 09 47 05 04 35 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
ማሳሰቢያ፡– ለአንድ ተመሳሳይ የጭነት መስመር የተሞላው ዋጋ ለተመላሹም ያገለግላል።