Addis Zemen (Oct 26, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
ሪች ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ ከፕላን ኢንተርናሽናል ጋር በአጋርነት በሚሠራው ፕሮግራም በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በሲዳማ ክልል በዳራ ወረዳ ለሚያስገነባው የተማሪዎች መማሪያ ክፍል እና የመጸዳጃ ቤት ግንባታ ሥራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት፡–
1. በ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው
2. Gc-6/BC-5ደረጃ እና በላይ ከከተማ ልማት ሚኒስቴር የተመዘገቡና ፍቃድ ያሳደሱ
3. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ
4. ከመንግሥት የሚፈለግበት ግብርና ታክስ ዕዳ አለመኖሩን የሚገልጽ ለበጀት ዘመኑ ብቻ የሚያገለግል የስምምነት ደብዳቤ ከሚመለከተው የታክስ አስተዳደር ቢሮ ማቅረብ የሚችል
5. ወርሃዊ የታክስ ማሳወቂያ በማቅረብ የተሰበሰቡትን ተጨማሪ እሴት ታክስ ገቢ ማድረጋቸውን የሚገልጽ ከሚመለከተቻው ገቢዎች የተሰጠ የማረጋገጫ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ
6. የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችሉ
7. ተጫራቾች የጨረታውን ዋጋ 2% ሲፒኦ በማሠራት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ከላይ ከተራ ቁጥር 1-7 የሚያሟሉ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 2000/ሁለት ሺህ ብር ብቻ/ በድርጅቱ ስም ገቢ በማድረግ ደረሰኝ በመውሰድ የማስረጃዎቻቸውን ኦርጅናል ይዞ በመቅረብ በመመዝገብ ኮፒውን በማስያዝ ከድርጅቱ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ የሚችሉ ሲሆን አንድ ኦርጂናልና ሁለት በፎቶ ኮፒ ማሽን ኮፒ የተደረጉ ሰነዶችን እያንዳንዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7/ሰባት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር ከጠዋቱ 2:30-6:30 ከሰዓት ከ7:30-11:30 ሰዓት ድረስ ዲላ በሚገኘው ሪች ዘ ኒዲ (RTN) ኢትዮጵያ ዋና ጽ/ቤት ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም
- በሰነዱ ላይ የፕሮጀክቱን አገልግሎት ዋጋ በአኃዝና በፊደል በግልጽ መጻፍ ይኖርባቸዋል፡፡
- በኦርጅናል ሰነዱ ላይ ማንኛውንም ዓይነት ስርዝ ድልዝ ሳይኖር በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ የተቋራጩ ማህተምና ፊርማ ማረፍ አለበት፡፡
- በእጅ የተሞሉ ኮፒ ሰነዶችን ማቅረብ ከጨረታው ውጪ ያደርጋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ8ኛው ቀን ከቀኑ 6:30 ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት በድርጅቱ ቢሮ ይከፈታል፡፡ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ይከፈታል፡፡
- አንዱ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
- ከላይ የቀረቡትን መስፈርቶች ሳያሟሉ የሚያቀርቡ ተቋራጮች ከጨረታው ውድድር ውጪ ይሆናሉ፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
|
ተ.ቁ |
የግንባታው ዓይነት |
LOT |
ግንባታው የሚገነባበት ወረዳና ቀበሌ |
|
1 |
1-ብሎክ ባለ 4-ክፍል የተማሪዎች መማሪያ እና 6-ክፍል ያለው 1- መጸዳጃ ቤት |
LOT 1 |
ሳቴ ሀንጋላ ቀበሌ /ዳራ ወረዳ ( Sate hangela Dara) |
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 046 331 0049 / 046 331 3145
ሪች ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ