በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የበሻሌ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የበሻሌ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Oct 27, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019

በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የበሻሌ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የ1ኛ ዙር ጥቅል ግዥ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አውጥቶ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

 

የዕቃ ዝርዝር

የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ

ሎት 1

አላቂ የትምህርት ዕቃ

44,000

ሎት 2

አላቂ የቢሮ እቃ

9000

ሎት 3

የፅዳት ዕቃ

30,000

ሎት 4

ለህንፃ ቁሳቁስና ተገጣጣሚዎች መግዣ

8200

ሎት 5

የደንብ ልብስ

28,000

ሎት 6

ለአላቂ የህክምና እቃ

400

ሎት 7

ህትመት

4600

ሎት 8

ፕላንትና ማሽነሪ መግዣ

14000

ሎት 9

ልዩ ልዩ መሳሪያዎች እና መፃህፎች

1800

ሎት 10

ካፌ

20,000

ሎት 11

የመኪና ኪራይ

9000

ሎት 12

የልብስ ስፌት

6000

ሎት 13

ፕላንትና ማሽነሪ ጥገና

1300

ሎት 14

ለምርምርእና ለልማት አላቂ እቃዎች

18,000

ስለሆነም መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች ቀርበው ወዳደር ይችላሉ።

1.ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብር ለመክፈላቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

3. የታደሰ ንግድ ፋቃድ ያለዉ።

4. ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

5. ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 4 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከዋጋ ማቅረቢያ አርጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር ከላይ የተዘረዘሩት እቃዎች ለእያንዳንዳቸዉ የዋጋ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የበሻሌ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በመቅረብ መግዛትና መጫረት ይችላሉ።

8. ተጫራቾች ዋጋ የሞላበትን ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ ብለው በመለየትና በ 2 ፖስታ በማሸግ እንዲሁም የተጠቀሱትን ማስረጃዎች አሟልተው የበሻሌ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 5 ውስጥ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 የሚከፈት ይሆናል።

9. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በር መምህርት ቢሮ ይከፈታል።

10. ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በቀኑ ባይገኙም ጨረታው የሚከፈት ይሆናል።

11. በጨረታ አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ጠቅላላ ዋጋ 10%የውል ማስከበሪያ በማስያዙ ከት/ቤቱ ጋር የግዥ ውል ስምምነት ይኖርባቸዋል።

12. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ ሳምፕል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

13. አሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፋዋቸውን ዕቃዎች በራሳቸዉ ትራንስፓርት ወደ መስሪያ ቤቱ የበሻሌ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ቡድን መሪ ድረስ ማቅረብ አለባቸዉ።

14. ተጫራቾች በጨረታው ላይ ቅሬታ ካላቸው የጨረታው አሸናፊው ከተለየበት ቀን ጀምሮ በ7 የሥራ ቀናት ውስጥ ቅሬታቸውን ለጨረታ ኮሚቴ በጽሁፍ ማቅረብ አለባቸው።

15. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሲያቀርቡ ቫት ያጠቃለለና ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች አሟልተው የበሻሌ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስና ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 5 – ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ብቻማስገባት ይኖርባቸዋል።

16. ሁለት ተወዳዳሪዎች ለአንድ ዕቃ ተመሳሳይ ዋጋ ቢያቀርቡ ኮሚቴው በጥራት ወይም ሌላ የቴከኒክ መስፈርት በመጠቀም አሸናፊ ይለያል።

17. ሁሉንም መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች በዋጋ ወይም በጥራት አሸናፊው የሚለይ ይሆናል።

18. መ/ቤቱ አሸናፊውን ተጫራች በሚመርጥበት ጊዜ የሚገዛውን ዕቃ ወይም አገልግሎት ብዛት ወይም መጠን እንደ አስፈላጊነቱ እስክ 20% ለመቀነስ ወይም ለመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።

19. አሸናፊው ድርጅት የግዥ መጠየቂያ ወይም (Purchase Order) ከደረሳቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ማቅረብ የሚችሉና የሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች እስቶክ ላይ ያሉ መሆን አለባቸው።

20. አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት መጫረት የምትችሉት የንግድ ፍቃዳችሁን ኮፒ በማድረግ ይዛችሁ ማምጣት ስትችሉ ነው። (በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በግዥ አፈፃጸም መመሪያ ላይ ለአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት ባወጣው መመሪያ መሰረት ነው።)

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 668 2902/ 011 667 9163 ወይም በአካል በሻሌ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ስሚት ሳፋሪ ቦሌ ምድብ ችሎት ፍርድ ቤት አጠገብ ፋይናንስ ቡድን መሪ ቢሮ በመቅረብ መጠየቅ ይቻላል።

የበሻሌ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት