የሰበታ ክ/ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለሰበታ ክ/ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የግንባታ ማሽነሪዎች፤ የደረቅ ጭነትና የሰው ደብል ገቢና ፒካፕ መኪናዎች ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የሰበታ ክ/ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለሰበታ ክ/ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የግንባታ ማሽነሪዎች፤ የደረቅ ጭነትና የሰው ደብል ገቢና ፒካፕ መኪናዎች ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል


Addis Zemen (Oct 29, 2026)

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የሰበታ ክ/ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለሰበታ ክ/ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የግንባታ ማሽነሪዎች፤ የደረቅ ጭነትና የሰው ደብል ገቢና ፒካፕ መኪናዎች ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ስለሚፈልግ ህጋዊ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው የተጫራቾች መመሪያ መሠረት ጨረታውን እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል፡፡

ዝርዝር ሁኔታዎች

የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከሰበታ ክ/ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 5000 (አምስት ሺህ ብር) በሲንቄ ባንክ ሂሳብ ቁጥር በ “sebeta Sub clty Finance office “A” 1064814111214″ የማይመለስ ብር ገቢ በማድረግ ዲፖዚት ሲልፑን/ Deposit slip/ ከሰበታ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት የአንድ መስኮት አገልግሎት /መሶብ/ ወደ ገቢ ደረሰኝ በማስቀየር የጨረታ ሰነዱን ከሰበታ ክ/ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የክፍለ ከተማ G+5 ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ ላይ ከሚገኘው የግዥ፣ ንብረት አስተዳደር አወጋገድ እና ጠቅላላ አገልግሎት የስራ ሂደት ክፍል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የተጫራቾች ግዴታዎች

1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ በስማቸው ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለዚሁም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው እና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ ፡፡

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ እና /TIN/ ተመዝጋቢና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው እንዲሁም በፌዴራል ገ/ሚኒስቴር ወይም ኦሮሚያ ገ/ ቢሮ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረ CPO (ሲፒኦ) ብቻ ብር 150,000.00 በ “Sebeta Sub city Finance office” ስም ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡

5. በማሽነሪና መኪና ኪራይ ላይ የሚሳተፉ ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ነዳጅ፤ ቅባት፤ ጥገናውን እና ሌሎች ተዛማጅ ወጪዎችን በተጫራቹ ድርጅት (አከራይ) የሚሸፈን ይሆናል፡፡

6. ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ ማሽነሪዎችንና መኪናዎችን በራሳችሁ ወጪ መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው ቦታ (ሥራ የሚሠራበት ቦታ) ድረስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

7. ተጫራቾች በጨረታው ላይ የሚያቀርቡት ማሽነሪና መኪና ደረጃውን የጠበቀ ሆኖ የባለቤትነት ማስረጃ ወይም ሊብሬ ወይም ህጋዊ የክራይ ውል አያይዞ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

8. አሸናፊ የሆኑ ተጫራች ውል ሲፈርሙ የውል ማስከበሪያ (ዋስትና ብር 250,000/ሁለት መቶ ሃምሳ ሺብር/ በ “Sebeta Sub clty Finance office” ስም አዘጋጅቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

9. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት ኦርጅናል እና ኮፒ በመለየት በፖስታ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን የመንግስት ሥራ ሰዓት ሰበታ ክ/ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የክፍለ ከተማ G+5 ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ ግዥ ንብረት አወጋገድ እና አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት የስራ ሂደት ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

10. ጨረታው በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰአት ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰበታ ክ/ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡

11. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

12. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች፡– 0113 384 292 በመደወል መረዳት ይችላሉ።

የሰበታ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *