በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኩታበር ወረዳ ፍ/ቤት አላቂ የጽሕፈት መሳሪያዎች፣ ቋሚ እቃ፣ የቢሮ ማሽነሪ፣ ህትመት፣ የደንብ ልብስ እና አላቂ የፅዳት እቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኩታበር ወረዳ ፍ/ቤት አላቂ የጽሕፈት መሳሪያዎች፣ ቋሚ እቃ፣ የቢሮ ማሽነሪ፣ ህትመት፣ የደንብ ልብስ እና አላቂ የፅዳት እቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 02, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኩታበር ወረዳ ፍ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በጋዜጣ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን

  • ሎት 1 አላቂ የጽሕፈት መሳሪያዎች
  • ሎት 2 ቋሚ እቃ
  • ሎት 3 የቢሮ ማሽነሪ፣
  • ሎት4 ህትመት፣
  • ሎት 5 የደንብ ልብስ፣
  • ሎት 6 አላቂ የፅዳት እቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፡፡

4 የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ/ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

6 የሚገዙ እቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (specfication) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በኩታበር ወረዳ ፍ/ ቤት ግዥ/ን/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 10 ከ27/2/019 ዓ.ም ጀምሮ መግዛት ይችላሉ፡፡

8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲ.ፒ.ኦ. ለሚወዳደሩበት ብር ወይም ለሚሰራው ስራ ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም ከታመነበት በባንክ በቼክ ማስያዝ አለባቸው::

9.ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡንም ኦርጂናልና ኮፒ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በኩታበር ወረዳ ፍ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 10 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ቀን ከ27/2/2019 ዓም ጀምሮ እስከ 18/3/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡

10, ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 10 በቀን 18/3/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ይከፈታል ተጫራቾች ለእቃው ዓይነትም ሆነ መጠን በጨረታው በሙሉ ወይም በከፊል መሳተፍ ይችላሉ፡፡ሆኖም አንድ ተጫራች በአንድ ሎት ውስጥ ከተዘረዘሩት የእቃ ዓይነቶች መካከል ከፋፍሎ መጫረት አይችልም፡፡

11. መ/ቤቱ ጨረታውን በድምር ወይም በነጠላ ዋጋ የማወዳደር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ጨረታው በመሰረዙ ምክንያት ተጫራቾች ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ሃላፊነት አይወስድም፡፡

12- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈለጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥ 09 14 068 901 ወይም 09 20 79 43 36 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት
የኩታበር ወረዳ ፍ/ቤት