የድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ለቢሮ መገልገያ የሚውሉ አላቂ የጽህፈት መሳሪያና የጽዳት እቃዎችን (ለ2ኛ ጊዜ) እና የህትመት ስራዎችን (ለ2ኛ ጊዜ) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት/ማሰራጫት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ለቢሮ መገልገያ የሚውሉ አላቂ የጽህፈት መሳሪያና የጽዳት እቃዎችን (ለ2ኛ ጊዜ) እና የህትመት ስራዎችን (ለ2ኛ ጊዜ) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት/ማሰራጫት ይፈልጋል


Melekite Dire (Oct 28, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር ድ/ዳ/አስ/ከ/ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ /003/2019

የድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ

  1. ለቢሮ መገልገያ የሚዉል አላቂ የጽህፈት መሳሪያና የጽዳት እቃዎችን (ለ2ተኛ ጊዜ)
  2. የህትመት ስራዎች (ለ2ተኛ ጊዜ)

ከዚህ በታች የተገለጸውን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሰራት ይፈልጋል

በዚህም መሰረት ከዚህ በታች በዝርዝር የተገለጹትን መሰፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

በዘርፉ ለ2019 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፣

የንግድ ዋና ምዝገባ የምስክር ወረቀት የሚያቀርብ፣

የተጨማሪ እሴት ታክስ / ቫት/ ተመዝጋቢ የሆነ ለዚህም የምስክር ወረቀት የሚያቀርብ ፣

የታክስ መለያ ቁጥር /ቲን/ የምስክር ወረቀት የሚያቀርብ ሆኖ

የጨረታ ማስከበሪያ ለሁሉም የግዥ አይነቶች በእያአንዳንዳቸዉ ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር ብቻ/ በገንዘብ ወይም በሲፒኦ ማቅረብ አለበት

ከዚህ በላይ የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟላ ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በመልዕክተ ድሬ ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ቁጥር 203 ድረስ በአካል በመቅረብ የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ/ ብር ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላል።

ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በመልዕክተ ድሬ ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 /አስራ አምስት/ የስራ ቀናት የአየር ላይ ቆይታ በኋላ በ16ኛው ቀን በቢሮው የግ/ፋ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 203 ከጠዋቱ 3፡00 ላይ የጨረታ ሰነድ መቀበያ ሳጥኑ ተዘግቶ /ታሽጎ/ በዚያኑ እለት ከጠዋቱ 3:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሚውለው ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከዚህ በላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ጨረታው የሚከፈት ይሆናል።

ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ ማብራሪያ የድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ቁጥር 203 ወይም በስልክ ቁጥሮች 02521309/ 0994013209/0928218374 ላይ በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል።


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *