በደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር ደ/ታቦር ከተማ የሚገኘው የጎሕ ሁለገብ የገበ/ህ/ስ/ማ/ዩንየን ኃ.የተ. በዞኑ ውስጥ ከሚገኙ ወረዳዎች ወደ ደ/ታቦር፣ ነፋስ መውጫ፣ ወረታ፣ አዲስ ዘመን፣ ሀሙሲት እና መካነ እየሱስ የኢንዱስትሪ ምርቶች (ስኳር፣ ዘይት…ወዘተ) እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ሌሎች ምርቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማጓጓዝ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር ደ/ታቦር ከተማ የሚገኘው የጎሕ ሁለገብ የገበ/ህ/ስ/ማ/ዩንየን ኃ.የተ. በዞኑ ውስጥ ከሚገኙ ወረዳዎች ወደ ደ/ታቦር፣ ነፋስ መውጫ፣ ወረታ፣ አዲስ ዘመን፣ ሀሙሲት እና መካነ እየሱስ የኢንዱስትሪ ምርቶች (ስኳር፣ ዘይት…ወዘተ) እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ሌሎች ምርቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማጓጓዝ ይፈልጋል


Be'kur (Nov 02, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር ደ/ታቦር ከተማ የሚገኘዉ የጎሕ ሁለገብ የገበ/ህ/ስ/ማ/ዩኔዬን ኃ.የተ. በዞኑ ውስጥ ከሚገኙ ወረዳዎች ወደ ደ/ታቦር፣ ነፋስ መውጫ፣ ወረታ፣ አዲስ ዘመን፣ ሀሙሲት እና መካነ እየሱስ የኢንዱስትሪ ምርቶች (ስኳር፣ ዘይት…ወዘተ) እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ሌሎች ምርቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሁሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የተሰማሩና የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  2. ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3.  ተጫራቾች ቢያንስ 200 ኩ/ል እና በላይ መጫን የሚችል መኪና ያላቸዉ እና የመኪናዉን የሊብሬ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ (ዋስትና) ወይም በጥሬ ገንዘብ ሆኖ የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ ጎሕ ሁለገብ የገ/ህ/ስ/ማ ዩኒዬን ኃ.የተወሰነ በሚል ስም በማሰራት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. የአገልግሎት ግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እንዳይሰበሰብባቸው ፈቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና (ሲፒኦ) ሲያሲይዙ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ ቫት የሚጠይቀው የአንዱ ወይም በጥቅል (ሎት) የሚገዛው እቃ እንጅ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አለመሆኑ ተወዳዳሪዎች ማወቅ አለባቸው፡፡
  6.  የምርቶቹ መጠን (ብዛት) በጨረታ ሰነዱ በዝርዝር ይገለፃል፡፡
  7.  ተጫራቾች የሚያጓጉዙበትን ቦታ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ እና የተጫራቾች መመሪያውን በማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ከጎሕ ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተወሰነ ከፍሎ በመግዛት ወይም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000561188126 ገቢ በማድረግ ኦርጅናል የባንክ አድቫይስ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሰነዱ ላይ የመወዳደሪያ ዋጋ፣ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-6 የተዘረዘሩትን ሰነዶች ሞልተው በፖስታ በማሸግ በዩኒዬኑ ቢሮ በደ/ታቦር በጣይቱ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 01 ፀደይ ባንክ ደ/ታቦር ዲስትሪክት ህንጻ 1ኛ ፎቅ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ የጨረታ ሰነዱ ተሸጦ በ10ኛው ቀን መጨረሻ 8፡30 ታሽጎ 8፡40 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡ ሆኖም 10ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
  10. አሸናፊው የሚለየው በተናጠል ዋጋ ሆኖ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ይሆናል፡፡
  11. አሸናፊዉ በተለየ በ5 ቀን ዉስጥ የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ጥሬ ገንዘብ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ዉል መዉስድ ይኖርበታል፡፡
  12. አሸናፊው ድርጅት (ግለሰብ) ንብረቱን ለማጓጓዝ ከተረከበ በኋላ ካሸነፈበት የዩኒየኑ ማዕከል (መጋዝን) ድረስ ሳይጎድል፣ ሳይበላሽ እና ሳይጠፋ የንብረቱን ደህንነት ጠብቆ የማስረከብ ግዴታ አለበት፡፡
  13. የመጫረቻ ዋጋዉ ዉል ከተወሰደበት ቀን ጀምሮ ለ6 ተከታታይ ወራት ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
  14. ዩኒዬኑ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. ዪኒየኑ ከሚያጓጓዘው ውስጥ 20 በመቶ የመቀነስ ወይም የመጨመር መብት አለው፡፡
  16. ሌሎች በዚህ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ጉዳዮች በኀብረት ሥራ ማህበራት ግዥና ሽያጭ አፈፃፀም መመሪያ መሰረት ይስተናገዳሉ፡፡
  17. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 441 13 36 /058 141 99 27 ደዉለዉ መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ጎሕ ሁለገብ የገበ/ህ/ ስ/ማህበራት ዩኒየን ኃ.የተወሰነ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *