በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን በሊቦ ከምከም ወረዳ የአዲስ ዘመን መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለሚፈልጋቸው የጽ/መሳሪያ (ሎት 1)፣ የጽዳት ዕቃዎች (ሎት 2)፣ ሌሎች አላቂ ዕቃዎች (የመብራት አምፖል እና የውሀ እቃዎች – ሎት 3) እና የህትመት አገልግሎት ግዥ (ሎት 4) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን በሊቦ ከምከም ወረዳ የአዲስ ዘመን መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለሚፈልጋቸው የጽ/መሳሪያ (ሎት 1)፣ የጽዳት ዕቃዎች (ሎት 2)፣ ሌሎች አላቂ ዕቃዎች (የመብራት አምፖል እና የውሀ እቃዎች – ሎት 3) እና የህትመት አገልግሎት ግዥ (ሎት 4) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Be'kur (Nov 02, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን በሊቦ ከምከም ወረዳ የአዲስ ዘመን መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

  • ሎት1. የጽ/መሳሪያ፣
  • ሎት 2. የጽዳት ዕቃዎች፣
  • ሎት 3. ሌሎች አላቂ ዕቃዎች (የመብራት አምፖል ሎት 3.1. የውሀ እቃዎች፣
  • ሎት 4. የህትመት አገልግሎት ግዥ አቅርቦቶችን በግልጽ ጨረታ ከአቅራቢዎች መካከል አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

 ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1.  በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2.  የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3.  የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ተመዝጋቢ የሆኑ ፡፡
  4. የግዥ መጠን ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በላይ ለሆኑ ግዥዎች የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ
    መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ
    ኦርጅናል ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ እያንዳንዱን ሎቶች ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ከግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 9 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የዕቃውን (አገልግሎት) ግዥ የተጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ኮፒውን ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአ/ዘመን መ/ደ/ሆስፒታል በግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡ/መሪ ቢሮ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10.  ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት (በሌሉበት) በሆስፒታሉ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 01 በ11ኛው ቀን በ3:15 ይከፈታል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ (በከፊልም) የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ በህግ የተከለከለ ነው፡፡መ/ቤቱ በጨረታ ዋጋ መጠን ላይ እስከ 20 በመቶ የመቀነስና የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግ/ፋ/ንብ/አስ/ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 444 03 71 /09 18 02 46 84 /09 18 61 70 63 /09 49 65 55 86 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአዲስ ዘመን መጀመሪያ ደረጃ
ሆስፒታል