የመኪና የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ – test3.diretenders.com

የመኪና የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


Addis Zemen (Nov 04, 2026)

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት አልማዝ ፈንቅል እና በፍ/ባለዕዳ መልሰው ከበደ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/111815 በ7/10/2016 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/111815 በ1511/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ሲሳይ ዓለሜ ጓደኞቹ የመኪና ማቆሚያ ቦታ የሚገኝ የሰ/ቁ ኮድ 2- 82686አ.አ Dx TOYOTA አውቶሞቢል የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 223,146 ( ሁለት መቶ ሃያ ሶስት ሺህ አንድ መቶ አርባ ስድስት ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 16 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፈደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎ ብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበትቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት/ስም CPO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዞወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

በፌ/ ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *