Addis Zemen (Nov 04, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የላሊበላ ከተማ አስር ገንዘብ ጽ/ቤት ለከተማ አስተዳደሩ በተፈቀደ የሥራ ማስኬጃ በጀት ለሲክተር መ/ቤቶች አግልግሎት የሚውል
- የጽህፈት መሳሪያዎች፣
- የጽዳት እቃዎች፣
- የእንስሳት ህክምና መድኃኒትና እቃዎች ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
- የደንብ ልብስ ጣቃ ጨርቅ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማ፣
- የስፖርት ትጥቅ/ የስፖርት እቃዎች
- የቀላል መኪና ጎማና
- የቀላል መኪና መለዋወጫ እቃዎች፣
- የህንፃ መሳሪያዎች፣ እንጨት፣ አሽዋና ድንጋይ፣ ብሎኬት ግዥ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎች በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በግልጽ ጨረታ በሎት በጥቅል አወዳድሮ ከአሸናፊው ጋር ውል በመያዝ መግዛት ይፈልጋል፡፡
1. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ የግብር ክሊራንስ ማስረጃ፣ የንግድ ፈቃዱን በጀርባው ያለውንም ጭምር ኮፒ በማድረግ እንዲሁም ለእንስሳት መድኃኒት አቅራቢ ከተጠቀሱት ማስረጃዎች በተጨማሪ የሙያ የምስክር ወረቀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2 የጨረታው ጠቅላላ የገንዘብ መጠን ከብር 500,000 በላይ ከሆነ የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው
3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 25/02/2019 ዓ.ም እስከ 04/03/2019 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጽ/ቤታችን ቢሮ ቁጥር 9 ድረስ በመምጣት የእያንዳንዱን ሎት የጨረታ ሰነድ በብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመግዛት መውሰድ ይችላል።
4. ተጫራቾች የጨረታ ሀሳባቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በላሊበላ ከተማ አስ/ር ገንዘብ ጽቤት ጨረታ ኮሚቴው ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 11ኛው ቀን ጥቅምት 05/3/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በዛው ቀን 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
5 ከላይ የተጠቀሰው የጨረታ የመክፈቻ ቀን ካላንደር ዝግ /ቅዳሜና እሁድ/ ከሆነ የመክፈቻው ቀን ለሚቀጥለው የስራ ቀንና ሰዓት ይተላለፋል
6 የጨረታውን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
7 ለደንብ ልብስ በጽ/ቤቱ የተዘጋጁ ናሙናዎችን በአካል በማየት ዋጋ መውላት ይቻላል
8 ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ
- ለጽህፈት መሳሪያዎች ብር 20,000፣
- ለጽዳት እቃዎች ብር 2,000፣
- የእንስሳት ህክምና መድኃኒትና እቃዎች ብር 5,000፡
- ለኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ብር 7,000፡ ብር
- ጣቃ ጨርቅ ብር 7,000፤
- የተዘጋጁ አልባሳት ብር 8,000፡
- ጫማ ብር 10,000፣
- የስፖርት ትጥቅ ብር 7,000
- የስፖርት እቃዎች ብር 3,000፣
- ለቀላል መኪና መለዋወጫ እቃዎች ብር 10,000፣
- የቀላል መኪና ጎማ ብር 30,000
- የህንፃ መሳሪያዎች ብር 3,000፣
- እንጨት ብር 1,000፣
- አሸዋና ድንጋይ ብር 2,000
- ብሎኬት ብር 1,300 በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ሲፒኦ/ ማቅረብ አለባቸው።
9 ለሁሉም ግዥዎች የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።
10. አሸናፊው አካል የሚያሸንፍበትን እቃ በላሊበላ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በራሱ ትራንስፖርት ከሚፈል ገው ቦታ ድረስ አጓጉዞ ማቅረብ ይኖርበታል።
11. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃ ኪው አር ደረሰኝ ያሳተሙ ወይም ካሽ ሪጅስተር የሚጠቀሙ መሆን አለባቸው።
12. ተጫራቾች ከዚህ በፊት የጨረታ አሸናፊ ሆነው እንደውላቸው ያላጠናቀቁ ወይም ከታወቀ ተቋም ዕገዳ የተደረገባቸውን አያካትትም።
13. ተጫራቾቹ በጨረታው ላይ ማብራሪያ ወይም ማሻሻያ ጥያቄ ካላቸው የጨረታው የጊዜ ገደብ ከማለቁ ከ3 ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው።
15. ተጫራቾቹ ስለጨረታው ዝርዝር ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0333361142/ 0333361143/033361169 በመደወል ማግኘት ይቻላል።
የላሊበላ ከተማ አስ/ር ገንዘብ ጽ/ቤት