Addis Zemen (Nov 11, 2026)
የመጀመሪያ ዙር የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር፣ ሲ/መ/ባ/005/2019
የሰርቪስ መኪና ኪራይ አገልግሎት ግዥ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
መ/ቤታችን በሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን ለ2019 በጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ የመንገድ ግንባታና ጥገና ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ደብል ጋቢና 1 ሚኒ ጋቢና እና አይሱዙ መኪናዎችን ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡
|
ሎት |
የመኪናው አይነት |
ብዛት |
ጠቅላላ ተሽከርካሪ የሥራ ቀን |
የሥራ ቦታ
|
|
1 |
ደብል ጋቢና |
4 |
1080 |
በሲዳማ ክልል ለሰሜናዊ ዞን |
|
ሚኒ ጋቢና |
4 |
1080 |
||
|
2 |
ደብል ጋቢና |
4 |
1080 |
በሲዳማ ክልል ለማዕከላዊ ዞን |
|
ሚኒ ጋቢና |
4 |
1080 |
||
|
3 |
አይሱዙ |
3 |
810 |
በሲዳማ ክልል ለሰሜናዊ ዞን |
|
4 |
አይሱዙ |
3 |
810 |
በሲዳማ ክልል ለማዕከላዊ ዞን |
|
5 |
አይሱዙ |
3 |
810 |
በሲዳማ ክልል ለደቡባዊ ዞን |
|
6 |
አይሱዙ |
3 |
810 |
በሲዳማ ክልል ለምስራቃዊ ዞን |
በዚሁ መሠረት፡–
1. ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚያስችለውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የታደሰ የንግድ ሥራ ወይም የአገልግሎት የሥራ ፍቃድ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸውን የሚያሳይ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ ቀናት ከባለሥልጣኑ መ/ቤት ግዥ የፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር -5 ቀርበው መግባት ይችላሉ
3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና (unconditional Bid) ከጠቅላላው ዋጋ ከ50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ/ CPO ወይም ባንከ ጋራንት በማሠራት ለብቻው በማሸግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለ120 ቀን ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።
4.የስሪት ዘመናቸው ለሚኒ ጋቢና፣ ደብል ጋቢና እና አይሱዙ እ.እ.አ 2006 እና ከዚያ በላይ መሆን አለባቸው።
5. ከዚህ በፊት ከሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን ጋር ውለታ ገብቶ በአፈጻጸም ችግር ምክንያት ማስጠንቀቂያተሰጥቶት ማሽነሪዎችን ወደ ሥራ ያላስገባና ውላቸው የተቋረጠ መኪና አከራይ ድርጅት የጨረታ ሰነዱን መግባትም ሆነ መወዳደር አይችልም።
6. የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ /Bid Security/ ፋይናሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒ ሰነዶችን በተለያየ ፖስታ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ ተካተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሠነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት። ከላይ የተጠቀሰው ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የእረፍት ወይም የሕዝብ በዓል ቀን ሆኖ ከዋለ በቀጣይ በሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ የሚከፈት ይሆናል።
7.በጨረታ ሰነድ ላይ የተጠቀሱትን የጨረታ መመሪያ እና ሕጎች አለማክበር በመጫረቻ ሰነዶቻቸው በሁሉም ገጽ ላይ ማህተምና ፊርማ ያለማድረግ እና ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ ያለበት የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
8.ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ በባለሥልጣኑ መ/ቤት አዳራሽ ይከፈታል። የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም።
9. ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በክፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን መረጃ መጠቀም ይችላሉ።
ስልክ ቁጥር 0462-128 446
የሲዳማ መንግዶች ባለስልጣን /ሀዋሳ/