የኢትዮጵያ ባዮሜትሪክስ ማኅበር (Ethiopian Biometric Society) ለሂሳብ ምርመራ (ኦዲት) አገልግሎት ብቁ የሆኑ የኦዲት ድርጅቶችን አወዳድሮ መሾም ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ ባዮሜትሪክስ ማኅበር (Ethiopian Biometric Society) ለሂሳብ ምርመራ (ኦዲት) አገልግሎት ብቁ የሆኑ የኦዲት ድርጅቶችን አወዳድሮ መሾም ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 13, 2026)

የኦዲት ሥራ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ባዮሜትሪክስ ማኅበር (Ethiopian Biometric Society) በ1993 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ማኅበር ነው። ማኅበሩ ለሂሳብ ምርመራ (ኦዲት) አገልግሎት ብቁ የሆኑ የኦዲት ድርጅቶችን ለመጋበዝ ይህን ማስታወቂያ አውጥቷል። ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።

1. የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፤

2. በሙያ ብቃትና ሕጋዊነት ታውቀው በመንግሥት የተመዘገቡ፤

3. የዘመኑን ግብር ከፍለው የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፤

4. በኦዲቲንግ ሥራ ልምድ ያላቸው፤

5. የተመሰከረላቸው የሂሳብ አዋቂዎች ሰርተፊኬት

6. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው መሆን አለበት፡፡

ተወዳዳሪዎች ለኦዲት አገልግሎት የምታስከፍሉትን ዋጋና ሥራውን ሠርታችሁ የምታስረክቡበትን ቀን በመጥቀስ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የሙያ ደረጃችሁንና ሕጋዊነታችሁን የሚገልጹ ማስረጃዎች በማያያዝ ከታች በተጠቀሰው የማኅበሩ አድራሻ እንድታመለክቱ እናስታውቃለን።

አድራሻ፦ አዲስ አራት ኪሎ ንግድ ማዕከል፣

4ኛ ፎቅ፣

ቢሮ ቁጥር G-04-1

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ስልክ ቁጥር፦ 0993916717/0911418062

የኢትዮጵያ ባዮሜትሪክስ ማኅበር


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *