በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በከምባታ ዞን ዱራሜ ከተማ የሚገኘው ፀዳል ኃላፊነቱ የተወሰነ ሁለገብ ኅብረት ሥራ ዩኒየን የ2019/20/ የምርት ዘመን በልግና መሐር እርሻ አገልግሎት የሚውል የአፈር ማዳበሪያ በሃላባ ቁሊቶ ከተማና በዶዮገና ከተማ ከሚገኙ ማዕከላዊ መጋዘኖች ወደ ከምባታ ዞን ወረዳዎች ክላስተር ጣቢያዎች ማጓጓዝ የሚችሉ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ትራንስፖርት ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ማጓጓዝ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በከምባታ ዞን ዱራሜ ከተማ የሚገኘው ፀዳል ኃላፊነቱ የተወሰነ ሁለገብ ኅብረት ሥራ ዩኒየን የ2019/20/ የምርት ዘመን በልግና መሐር እርሻ አገልግሎት የሚውል የአፈር ማዳበሪያ በሃላባ ቁሊቶ ከተማና በዶዮገና ከተማ ከሚገኙ ማዕከላዊ መጋዘኖች ወደ ከምባታ ዞን ወረዳዎች ክላስተር ጣቢያዎች ማጓጓዝ የሚችሉ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ትራንስፖርት ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ማጓጓዝ ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 21, 2026)

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ፀዩ/001/2019

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በከምባታ ዞን ዱራሜ ከተማ የሚገኘው ፀዳል ኃላፊነቱ የተወሰነ ሁለገብ ኅብረት ሥራ ዩኒየን የ2019/20/ የምርት ዘመን በልግና መሐር እርሻ አገልግሎት የሚውል የአፈር ማዳበሪያ በሃላባ ቁሊቶ ከተማና በዶዮገና ከተማ ከሚገኙ ማዕከላዊ መጋዘኖች ወደ ከምባታ ዞን ወረዳዎች ክላስተር ጣቢያዎች ማጓጓዝ የሚችሉ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ትራንስፖርት ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ማጓጓዝ ይፈልጋል።

ስለዚህ ተጫራቾች ከዚህ በታች ከ 1 እስከ 8 የተዘረዘሩ መስፈርቶች አሟልተው በመቅረብ መወዳደር የሚችሉ መሆኑን በድጋሚ እናስታውቃለን።

1/ በዘርፉ ሕጋዊ፣ የታደሰ ፈቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር ስለመከፈሉ መረጃና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል

2/ ከፈቃድ ሰጪ የመንግሥት መ/ቤት የሚመለስ ዋናና የማይመለስ ኮፒ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል

3/ በዘርፉ የሠራበትን የምስጋና ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል

4/ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ CPO ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችል

5/ ጨረታውን የሚያሸንፍ ተጫራች የውል ማስከበሪያ ብር 250,000.00 ቅድሚያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በካሽ ማስያዝ የሚችል

6/ ተጫራቹ ለጭነት የሚያሰማራቸው ተሽከርካሪዎች ቢያንስ በአንድ ጊዜ 2000 ኩ/ል ማንሳት የሚችሉትን ዝርዝር መረጃ ፈቃድ ከሰጣው የመንግሥት መ/ቤት በተሽከርካሪ አይነት፣ የሰሌዳ ቁጥር፣ የመጫን አቅም የያዘ መረጃ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርበታል።

7/ ለአስተዳደር ያመች ዘንድ ማንኛውም ተጫራች በአንድ ወረዳ ካሉት ጠቅላላ ክላስተር የማራገፊያ ጣቢያዎች ውስጥ በከፊል ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ አይቻልም።

8/ ተጫራቹ ከማዕከላዊ መጋዘኖች እስከ ማራገፊያ የወረዳ ጣቢያዎች ያለውን ጠቅላላ የጠጠርና አስፋልት መንገድ ድምር ርቀት ላይ የአንድ ኪሎ ሜትር የወረዳው ኪሎ ሜትር የወረዳው አማካይ ነጠላ ዋጋ በእያንዳንዱ ማራገፊያ ጣቢያ ደረጃ ሞልቶ ማቅረብ ይኖርበታል።

ማሳሰቢያ

1/ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ የማይመለስ 1500 ብር /አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር/ በመክፈል የድርጅቱ ከብ ማህተም ያረፈበትን የጨረታ ሰነድ (የግዴታዎች ዝርዝር፣ ከማዕከላዊ መጋዘን እስከ ማራገፊያ ቦታ ያለው የጠጠርና አስፋልት መንገድ ርቀት፣ ለመንገዱ የሚያስፈልግ የተሸከርካሪ ዓይነትና የወረዳ ነጠላ አማካይ ዋጋ መሙያ) የያዘ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከቢሮ ቁጥር 5 መግዛት ይችላሉ።

2/ ተጫራቾች በሰም የታሸገ ኤንቨሎፕ /ፖስታ/ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ውስጥ በክብ ማህተማቸው የተረጋገጠ የጨረታ ሰነድ በድርጅቱ ዋና ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።

3/ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በድጋሚ ታትሞ ከወጣበት ቀን እንስቶ ባሉት ተከታታይ 7 የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ7ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ 11፡30 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ይታሸጋል። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በድጋሚ ታትሞ በወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 7 ተከታታይ የስራ ቀናት(ቅዳሜና እሁድን ሳያካትት) በ8ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት በዩኒየኑ ጽ/ቤት በይፋ ይከፈታል፡፡ ሆኖም 8ኛው ቀን ቅዳሜ ና እሁድ ላይ ከዋለ ቀጥሎ ባለው ቀን የስራ ቀን (ሰኞ) ጨረታው ከላይ በተገለጸው ሰዓትና ቦታ ይከፈታል፡፡ በጨረታው በሚከፈትበት ቀን የሚሳተፉ ወኪል ተሳታፊዎች ከወከላቸው ድርጅት ህጋዊ ደብዳቤና ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

4/ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነድ ጋር በአጫራቹ ድርጅት በማህተም ተረጋግጠው የተዘረዘሩ ግዴታዎችን ማሟላት ይጠበቅበታል።

5/ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

6/ አንዱ ተጫራች ሌላው ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ አይፈቀድም።

አድራሻ፡– ከምባታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት

ስልክ : 0913 478 832 / 0912 355 938 / 0992 001 000 / 0916 748 108

ፀዳል ኃላፊነቱ የተወሰነ ሁለገብ ህብረት ሥራ ዩኒየን

ዱራሜ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *