Addis Zemen (Nov 22, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት መንገዶች ባለስልጣን የሚዛን ዲስትሪክት ጽ/ቤት በተለያዩ ፕሮጀክቶች እና ጥገና ሳይቶች ለሚያከናውነው የመንገድ ጥገና እና ግንባታ ስራ የሚውል ዳም ትራክ (ገልባጭ መኪና) እና ሎደር በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዝርዝር መሠረት አቅራቢዎችን ይጋብዛል።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉ ከተከፈለበት አገልግሎት ጋር የተዛመደ የንግድ ሥራ ወይም አገልግሎት ስራ ፍቃድ ያለው ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ የንግድ ምዝገባ ሰርትፍኬት ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በተለያዩ ፖስታ ቴከኒካል እና ፋይናንሻል በማድረግ ኦርጅናል እና ኮፒ ተለያይቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰንዱን የማይመለስ 200(ሁለት መቶ ብር) በመክፈል አቅንብ አስተዳደር ቢሮ ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጠቅላላ ዋጋ 0.5% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንከ CPO(ሲፒኦ)ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 6፡30 ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡ ጨረታው በዚያው ቀን ከቀኑ 8፡30 ድረስ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን እለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡—0917906864 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት መንገዶች ባለስልጣን የሚዛን ዲስትሪክት ጽ/ቤት