በድሬዳዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት በአስተዳደሩ ስር ላሉ ተቋማቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸሮችን በስትራቴጂክ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 23, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨ/መ/ቁ ግዥ/ን/ማ 512/የመ/ግ/ጨ/005/19 እና 512/የመ/ግ/ጨ/006/19

በድሬዳዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት በአስተዳደሩ ስር ላሉ ተቋማቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸሮች ግዢ በስትራቴጂክ ለመግዛት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያውን አውጥቶ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት፡-

1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው

2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

3. በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣

4. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የጨረታ ሠነዱን በፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ቁጥር 109 ቀርበው ለእያንዳንዱ ጨረታ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) መግዛት የሚችሉ ሲሆን በጨረታ መክፈቻው እለት የጨረታ ሠነዱን በትክክል ሞልተው ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዋናውንና ኮፒውን በአግባቡ አሽገው ማስገባትይጠበቅባቸዋል።

5. የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ላይ ታሽጎ በዛው ዕለት 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 215 በግልጽ ሲከፈት፤ ቀኑ በዓል ወይም የዕረፍት ቀናት ላይ ከዋለ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን።

6. ተጫራቾች ለኤሌክትሮኒክስ ግዢ ብር 350,000.00 (ሶስት መቶ ሃምሳ ሺ ብር) ፤ ለፈርኒቸር ግዢ ብር 150,000.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺ ብር) እና የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይንም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

7. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

8. ተጨማሪ ማብራሪያና መረጃ ቢያስፈልግ በሚመለከተው አድራሻ መጠቀም ይችላሉ። በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግለሎት

ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 215

የስልክ ቁጥር፡ 0915-76-19-64 / 0923-32-32-42

በድሬዳዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *