Be'kur (Nov 23, 2026)
የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ ደማ/02/2019፣
የጨረታ ዙር፡- 2ኛ የጨረታ ዓይነት፡- መደበኛ
የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር መሬት መምሪያ የከተማ ቦታን በሊዝ ለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ከ”ሀ” እስከ“ሠ” በተዘረዘረው መሰረት ለመኖሪያ እና ንግድ አገልግሎት የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል።
በመሆኑም መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል ከአገልግሎት አቅርቦት ተጠሪ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በስራ ሰዓት መግዛት የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን። በ10ኛው ቀን የጨረታ ሰነድ የሚሸጠው እስከ ቀኑ 10፡00 ብቻ ይሆናል።
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ብቻ ይሆናል።
- የጨረታ ሳጥን የሚታሸገው ማስታወቂያ በጋዜጣ በወጣበት በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ነው።
- ቦታውን መጎብኘት ለሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጉብኝት ፕሮግራም በውስጥ ማስታወቂያ የምናሳውቅ ይሆናል።
- ጨረታው የሚከፈተው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 በመምሪያው ግቢ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡ 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡።
- ስለጨረታው ዝርዝር ማብራሪያ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ የተጫረቱበትን የቦታ ስፋት በቦታው የመነሻ ዋጋ በማባዛት የሚገኘውን ዉጤት ከሀያ በመቶ ያላነሰ በዝግ አካውንት በማስገባት በባንክ የተመሰከረለት ሰነድ ከዋጋ እና የሃሳብ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በጨረታው ለተሸነፉ ተወዳዳሪዎች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተመላሽ የሚደረገው የጨረታው አሸናፊ ከተረጋገጠበት ከሚቀጥለው ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ይሆናል። መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር መሬት መምሪያ