Addis Zemen (Nov 27, 2026)
የምግብ ጥራጥሬ ማጣፈጫ እና የማገዶ እንጨት፤ የጨረታ ማስታወቂያ
- የጨረታ ቁጥር 1 ለህግ ታራሚዎች ምግብ አገልግሎት የሚውሉ ጥራጥሬዎች እንዲሁም አትክልትና ማጣፈጫዎች የማገዶ እንጨት፤
- ቁጥር-2- ለጥገናና ለግንባታ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ግብዓቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅቶች መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት፡-
1. ተጫራቾች በጨረታ ስመሳተፍ የሚፈልግ ሁሉ፣ በሥራው መስክ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በዕቃ ግዢ አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እንዲሁም ቲን ቁጥር (Tin Number) ተመዝጋቢ የሆኑና ግብር ስለመከፈሉ የተሟላ ማስረጃ ሊያቀርቡ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
2. ለህግ ታራሚዎች ለምገብ አገልግሎት የሚውሉ ጥራጥሬዎች እንዲሁም አትክልትና ማጣፈጫዎች የማገዶ እንጨት ለጨረታው የውል ማስከበሪያ ብር 60,000.00 (ስልሳ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
3. ተጫራቾች አንዱ በሌላው ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም።
4. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ (ፕሮፎርማቸው) በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በ4 ኮፒ አሽገሙ ማቅረብ አለባቸው።
5. የጨረታ ቁጥር 1 ህዳር 25/3/2019ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሰነዳቸውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የግዥ ክንውን ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው በዚሁ ዕለት ከረፋዱ 4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማረ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
6. የጨረታ ቁጥር 2- ህዳር 26/3/209 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሰነዳቸውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የግዥ ክንውን ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው በዚሁ ዕለት ከረፋዱ 4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማረ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
7. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ገላን ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል በሚገኘው ግ/ቤቶች ማስረከብ አለባቸው ማረ/ቤቱ የሚገዛቸው ዕቃዎች በጨረታ ሰነዱ ተዘርዝረው ቀርበዋል።
8. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ቃሊቲ በሚገኘው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000007971188 ቃሊቲ ማረ/ቤት እደ/ጥ/ማዕከል በሚል ገንዘቡን ገቢ ካደረጉ በኋላ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
9. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
10. ተጫራቾች ፕሮፎርማቸው ላይ ዋጋ ሲፅፉ ስርዝ ድልዝ የሌለበት መሆን ይገባዋል፤ ስርዝ ድልዝ ያለበት ዋጋ ተቀባይነት የለውም፤ በአሃዝ መፃፍ ይጠበቅባቸዋል።
11. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡- ገላን ከፍተኛ/ጥበ/ማረ/ማዕከል
የከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል