Addis Zemen (Nov 27, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የኦዳ የገበያ ማዕከል ግንባታ አክሲዮን ማህበር የማህበሩን የ4 ዓመት ሒሳብ በውጪ ኦዲተር በጨረታ አወዳድሮ ስማስመርመር ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል።
1. በቻርተር የተመሰከረለት የሒሳብ አዋቂ ደረጃ -3 እና ከዚያ በላይ የተፈቀደለት ኦዲተር መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. ከሚመለከተው ህጋዊ አካል የዘመኑን የብቃት ማረጋገጫ በክልሉ በሙያዉ ለመስራት የተሰጣቸውን ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ።
3. ተጫራቾች ከሁለት ያላነሱ ኮርፖሬሽኖችን ወይም በተፈቀደላቸው ደረጃ -3 ሒሳብ መመርመራቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
4. የታደሰ የስራ ፍቃድና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የ30,000 ብር CPO ወይም በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ማስያዝ የሚችሉ።
6. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዉስጥ የመወዳደሪያ ማስረጃዎቻቸውን በሰም በታሸገ ፖስታ /Envelope/ ለአክሲዮን ማህበሩ ጽ/ቤት እንዲያቀርቡ እናስታውቃለን፡፡
ተጨማሪ ማሳሰቢያ
- የጨረታ ሰነዶች ሙሉና ትክክል መሆን አለባቸው።
- የተሳሳተ ወይም ያልተሟላ ሰነድ ያቀረበ ተጫራች ከውድድር ሊሰረዝ ይችላል።
- ድርጅቱ በህግና በጨረታ ሂደቱ መሠረት ጨረታውን የመሰረዝ ወይም የማስተካካል መብቱን ይጠበቃል።
የጨረታው ሰነድ ገዢ የሚፈጸመው ሲቲ ሞል ህንጻ ፊት ለፊት ኪያ ባርና ሬስቶራንት ቢሮ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን ብር 500 የማይመለስ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
አድራሻ፡– በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በአሰላ ከተማ የኦዳ የገበያ ማዕከል ግንባታ አ/ማህበር
ኦዳ የገበያ ማዕከል ግንባታ አክስዮን ማህበር