የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተርሚናል ሁለት (2) ውስጥ የሚገኙ ከፍት ቦታዎችን ለተለያዩ አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 19, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የቦታ ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር: SSNT-T545

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተርሚናል ሁለት (2) ውስጥ የሚገኙ ክፍት ቦታዎችን ከዚህ በታች ለተጠቀሱ አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

  • ለባንከ እና ለውጭ ምንዛሬ አገልግሎት የሚውሉ ሁለት (2) ቦታዎች ተርሚናል 2 መዳረሻ( Arrival
  • ለኤትኤም/ATM አገልግሎት የሚውል ሁለት (2) ቦታዎች ተርሚናል 2 መዳረሻ (Arrival በመሆኑም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡

በባንከ አገልግሎት ስራ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ህጋዊ ፈቃድ እና የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው እና በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ጨረታ መክፈቻው አለት ድረስ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራች በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT T545 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ (Deposit Ship) ቅጂውን (scar copy) የጨረታ ቁጥር፣ የድርጅቱ ስም እና ስልክ ቁጥር ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላከ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡

በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ብር 100,000.00(አንድ መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ከኢንሹራንስ እና ቅደመ ሁኔታ ያለው ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋናውን እና ቅጂውን ቴከኒካል ሰነድ፣ ዋናውን እና ቅጂውን ፋይናንሻል ሰነድ እና የጨረታ ማስከበሪያ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል እስከ መስከረም 9 ቀን 2018 .. ከቀኑ 9:00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተመሳሳይ ቀን 930 ሰዓት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡ ለተጨማሪ ማብራሪያ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ

ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል

በስልክ ቁጥር፡ -25-15-17-89-18

ኢሜል: ESAYASTS@ethiopianairlines.com 

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *