Your cart is currently empty!
የሻሸመኔ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለነገሌ ቦረና ሰብስቴሽን የ33 ኪሎ ቮልት ብሬከሮች ማስቀመጫ ቤት ማስፋፊያ ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 19, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር EEU-SR/NCB/001/2018
የሻሸመኔ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለነገሌ ቦረና ሰብስቴሽን የ33 ኪሎ ቮልት ብሬከሮች ማስቀመጫ ቤት ማስፋፊያ ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ተጫራቾች፡–
1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡና በመስኩ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ፣ በኮንስትራክሽን ግዥ ድረ–ገፅ (http://www.ppa.gov.et ) ላይ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፤
2. ደረጃ አምስት (5) እና ከዛ በላይ የግንባታ ተቋራጭ /BC & GC/ ያለው ሆኖ በዘርፉ ተዛማጅነት ያለው አንድ የመልካም ሥራ አፈፃፀም፤ የክፍያ ሰርተፊኬት እና ውል ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው!
3. ከዚህ በፊት ከድርጅታችን ጋር ሥራ ሰርተው በወቅቱ ያላስረከቡ ኮንትራከተሮች በዚህ ጨረታ መወዳደር አይችሉም፤
4. በገቢዎች አስተዳደር ባለስልጣን በጨረታ ላይ መሳተፍ የሚያስችል ደብዳቤ ያላቸው እና ደብዳቤውን ማቅረብ የሚችሉ፤
5. የጨረታ ሠነዱን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሻሸመኔ ከተማ ብሔራዊ ሎተሪ ፊት ለፊት በሚገኘው ህንፃ፣ ሻሸመኔ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሰፕላይ ቼይን ንበረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ፣ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 በመቅረብ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፤
6. ለጨረታው ማስከበሪያ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ጋራንቲ ማቅረብ አለባቸው፤
7. የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ኮፒና ኦሪጅናል በማለት እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በመቅረብ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤
8. ጨረታው ነሐሴ 30 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8:30 ላይ ይከፈታል፣
9. ሪጅኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፈል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
10. ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር (046) 2113001) ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፤
11. ለሥነ ምግባር ደንቦች ለመግዛት የቃል ኪዳን ሰነድ /ቅጽ/ በመፈረም ከቴክኒካል ሰነድ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
የሻሸመኔ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት