Your cart is currently empty!
ስፋቱ 255 ካ/ሜ የሆነ ቤት የጨረታ ማስታወቂያ
Melekite Dire(Aug 20, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት አቶ ኢብራሂም ኡስማን አሊ እና በፍ/ባለእዳ አቶ አወድ ኡስማን አሊ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ጉዳይ በመዝገብ ቁጥር 100389 የተሰጠውን ውሣኔ ለማስፈፀም በድሬዳዋ ከተማ ቀበሌ 08 ክልል ውስጥ የሚገኝ በካርታ ቁጥር 3833 በቤት ቁጥር 4056 የሆነና ስፋቱ 255 ካ/ሜ የሆነና በሟች ወ/ሮ ፋጡማ ፋራህ የተመዘገበ ቤት በመነሻ ግምት ብር 1.552.468.43 /አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሃምሣ ሁለት ሺህ አራት መቶ ስልሣ ስምንት ብር 43/100 / በሆነ ዋጋ በኃራጅ ሸያል እንዲሸጥ የታዘዘ በመሆኑ ጥቅምት 1 ቀን 2018 ዓ.ም በጨረታ አወዳድሮ በኃራጅ መሸጥ አስፈልጓል፡፡ ስለሆነም በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡50 ድረስ ባለው ጊዜ የተጫራቾች ምዝገባ ንብረቱ በሚኝበት ቦታ የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው በተጠቀሰው ቀን እና ንብረቱ በማገኝበት ቦታ ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 5፡00 ባለው ጊዜ ይከናወናል።
በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ሁሉ ማንነታችሁን የሚያረጋግጥ መታወቂያ በመያዝ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ በመገኘት መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን ማንናውም ተጫራች ለሃራጅ ጨረታው ከመዝገቡ በፊት የጨረታውን መነሻ ዋጋ ¼ኛ ቀድሞ በ CPO በባንክ አስይዘው እንዲመዘገቡ CPO ያልያዘ ተጫራች እንዳይመዘገብ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ። የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ያሸነፈበትን ገንዘብ ¼ኛውን ወዲየውኑ በ CPO ወይም በሞዴል 85 በፍ/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል ማስያዝ አለባቸው፡፡ ቀሪውን ¾ኛ ገንዘብ ደግሞ ጨረታው በተካሄደ በ15 ቀናት ውስጥ አጠናቀው ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህ ባይሆን ቀድሞ የተያዘው ገንዘብ ለጨረታ የወጣው ወጪ ተቀንሶለት ቀሪው ለመንግስት ገቢ እንደሚሆን ሊገነዘቡ ይገባል፡፡
የድሬዳዋ ምድብ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ፍትሐብሄር 4ኛ ችሎት