Your cart is currently empty!
የድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ለ2018 በጀት ዓመት የጠላቂ ፓንኘ ሞተር የመጠቅለል የአገልግሎት ግዢ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Melekite Dire(Aug 20, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ለ2018 በጀት ዓመት የጠላቂ ፓንኘ ሞተር የመጠቅለል የአገልግሎት ግዢ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ፡- ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡-
- የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድና የአቅራቢዎች መታወቂያ ያላቸው፣
- ቫት የተመዘገቡ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ የሚያቀርቡ ቲን ቁጥር ያለው፡፡
- ከፋይናንስና ኢኮኖሚ ቢሮ የስራው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል ቅድሚያ ይሰጠዋል፡፡
- የጨረታው ዶክመንት የማይመለስ ብር 500 / አምስት መቶ / በመክፈል ድሬዳዋ አስተደደር ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ከግዥና ፋይናንስ ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 05 በጥሬ ገንዘብ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ሰነዱን መግዞት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ በውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ቢሮ ቁጥር 05 ከ1፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ዘወትር በሥራ ሰዓትና ቀን መግዛትና ማስገባት ይቻላል፡፡
- ጨረታው በማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን በ3፡00 ሰዓት የጨረታ ሣጥኑ ተዘግቴ በተመሳሳይ 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙት ጨረታው ይከፈታል።
- የጨረታው ዶክመንት በታሸገ ፖስታ የእያንዳንዱ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ በግልጽ ማስቀመጥ አለበት በተጨማሪ በጨረታ ዶክመንቱ ውስጥ የተዘጋጁት ፎርማት ተሞልተውና ተፈርመው መቅረብ አለባቸው ፣
- ያሸነፈው ተጫራች የተጠየቀውን አገልግሎት የግዥ ትእዛዝ እንደተሰጠው በእስፔስፊኬሽኑ እና በናሙናው መሠረት በ30 ቀናት ውስጥ በድሬዳዋ አስተደደር ውሃና ፍሣሽ ባለስልጣን በሚገኝበት መጋዘን አቅርቦ ማስረከብ አለበት ፡፡
- በዶክመንቱ ከተሰጠው ስፔስፊኬሽን ውጪ የሚቀርብ ተቀባይነት የለውም፣
- በጨረታው ሂደት ጨረታውን ለማዛባት ለማጭበርበር የሞከረ ተጫራች ከጨረታው ውጭ እንደሚሆንና በመንግስት ግዥ እንዳይሳተፍ ይደረጋል፡፡
- የጨረታ ሣጥኑ ከተዘጋ በኂላ የሚመጣ የጨረታ ዶክመንት ተቀባይነት የለውም፡፡
- ባለስልጣን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መመቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡- ድሬዳዋ አስተደደር ውሃና ፍሣሽ ባለስልጣን ቀበሌ 03 ድሮዳዋ ስልክ ቁጥር 025 11 222 4892 ፖ.ሣ.ቁ 446