የድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቢስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ በ 2018 በጀት ዓመት የመኪና እና የሞተር ሣይክል ጥገና ገራጅ በዘርፉ የተሰማሩትን ህጋዊ ጋራዦችን በግልፅ ጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል


Melekite Dire(Aug 20, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ 

የድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቢስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ በ 2018 በጀት ዓመት የመኪና እና የሞተር ሣይክል ጥገና ገራጅ በዘርፉ የተሰማሩትን ህጋዊ ጋራዦችን በግልፅ ጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡

  1. የመኪና እና የሞተር ሣይክል ጥገና ጋራጅ ግዥ

 ስለዚህም ፡-

  • ህጋዊ የ2017 የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈለና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ፣
  • የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የእቃና የአገልግሎት አቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡና ለዚህም የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
  • የግብር የመክፈያ ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢነት ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ፣
  • በተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፣
  • ከትራንስፖርት ባለስልጣን መስሪያ ቤት ለ2017 በጀት ዓመት የተሰጠ የጋራጅ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል ፣
  • ተጫራቾች ጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 / አምስት መቶ ብር / በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ የግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 210 በመቅረብ መግዛት የሚችል፣
  • ተጫራቾች ጨረታ ማስከበሪያ 3000. / ሶስት ሺህ ብር / በባንክ በተመሰከረለት ቼክ ( CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይ ማቅረብ የሚችል፣
  • ተጫራቾች በጨረታ ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸውና ውል ከፈፀሙ በኋላ ወዲያውኑ ስራ መጀመር ይኖርባቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች የሚጫረቱትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎኘ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት በስራ ሰዓት ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ በመቅረብ የሚወዳደሩበትን ዋጋ በመሙላት የጨረታ ሰነዱን በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4 ሰዓት ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  • ጨረታው በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ይታሸጋል። በዛው እለት ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል። ይህ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ይከፈልታል።

ማሣሰቢያ 

ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጨማሪ ማብራሪያና መረጃ በስልክ ቁጥር 09 41 47 27 41 መደወል ይችላሉ።


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *