የትግል ለነፃነት ቅድመ አንደኛ፤ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የደንብ ልብስና የወንድና የሴት ጫማዎች፣ አላቂ የጽዳት ዕቃዎች፣ የትምህርት የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የቢሮ አላቂ ዕቃዎች፣ የስፖርት ትጥቆች እና የስፖርት ዕቃዎች፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ የሕንፃ መሣሪያዎች እና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 20, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ 

የጨረታ ቁጥር ትለ 001/2018 ዓ.ም.

የትግል ለነፃነት ቅድመ አንደኛ፤ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

1/ የደንብ ልብስና የወንድና የሴት ጫማዎች

2/ አላቂ የጽዳት ዕቃዎች

3/ የትምህርት የጽሕፈት መሣሪያዎች

4/ የቢሮ አላቂ ዕቃዎች

5 የስፖርት ትጥቆች እና የስፖርት ዕቃዎች

6/ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች

7/ የሕንፃ መሣሪያዎች

8/ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች

ተጫራቾች ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉና የቫት የምዝገባ ወረቀት አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

1. ያሸነፉበትን ዕቃ ግዥ /ቤት ድረስ በራሳቸው ወጪ ማቅረብ የሚችሉ።

2. ተጫራቾች የአንዱን ዋጋ ሲያቀርቡ ከነቫቱ ደምረው ማቅረብ አለባቸው።

3. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት አለባቸው፡፡ ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ በመ/ቤቱ ሰነድ ላይ ብቻ መሆን አለበት።

4. የጨረታ ሰነዱ ማስገቢያ ቀን ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ይሆናል።

5. ጨረታውን ያሸነፈ ድርጅት ዕቃዎችን ማስረከብ ያለበት ማሸነፉ ከተነገረው 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ይሆናል።

6. የጨረታ ማስገቢያ /ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይሆናል።

7. የጨረታውን ሰነድ ከላይ በተራ ቁጥር 4 የተጠቀሰውን ገንዘብ በመክፈል በት/ቤቱ ፋይ/ ግን አስ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 መውሰድ ይቻላል።

8. ጨረታው በወጣ በአስራ አንደኛው ቀን 415 /አራት ሰዓት ከሩብ/ ታሽጎ 430 /አራት ሰዓት ተኩል/ በት/ቤቱ አዳራሽ ሕጋዊ ተጫራቾቻቸው ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል።

9. /ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለጨረታ ማስከበሪያ ብር ከታች የተገለጸውን በባንክ የተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለበት፡ የደንብ ልብስና የወንድና የሴት ጫማዎች ብር 3000 /ሶስት ሺህ/ የአላቂ የጽዳት ዕቃዎች ብር 5000 /አምስት ሺህ ብር/ የትምህርት እና የጽህፈት መሣሪያዎች ብር 5500 /አምስት ሺህ አምስት መቶ ብር/ የቢሮ አላቂ ዕቃዎች ብር 5000 /አምስት ሺህ/ የስፖርት ትጥቆች እና የስፖርት ዕቃዎች ብር 4000 /አራት ሺህ/ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ብር 3500/ሶስት ሺህ አምስት መቶ/ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ብር 4500 /አራት ሺህ አምስት መቶ/ የሕንፃ መሣሪያዎች ብር 3500 /ሶስት ሺህ አምስት መቶ/ እንዲሁም የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ብር 4000 /አራት ሺህ ብር/

አድራሻ፡ትግል ለነፃነት ቅድመ አንደኛና አንደኛ መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በየካ ከፍለ ከተማ በቀድሞ ቀበሌ 01/02 በአዲሱ ወረዳ 01 ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ሳይደርስ 800 ሲቀረው 41 ቁጥር አውቶብስ መሄጃ መስመር

ማሳሰቢያ፡ለጥራት 80% ለዋጋ 20% ስለሆነ ለጥራት ከምንም በላይ ቅድሚያ እንሰጣለን።

የአንዱን ዕቃ ዋጋ ስታቀርቡ ከነቫቱ ማቅረብ አለባችሁ።

ቫት ሳያካትት ዋጋ ያቀረበ ድርጅት ጨረታው ውድቅ ይሆንበታል።

ማንኛውንም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ሲያስገባ ሳምፕል ማቅረብ አለበት።

ማንኛውም ተጫራች መረጃ መጠየቅ ሲፈልግ በሥራ ቀናት ጠዋት 230-1130 ባለው ጊዜ ደውሎ መረጃ መጠየቅ ይችላል። ቅዳሜና እሁድ የእረፍት ቀናት ስለሆነ /ቤቱ ዝግ ነው።

ስልክ 0111541611/ 0118120047

ትግል ለነፃነት ቅድመ አንደኛ፣  አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት