በኢሉአባቦር ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት የዳሪሙ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ 2018 ዓ.ም የበጀት ዘመን በሥሩ ላሉት መሥሪያ ቤቶች ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 22, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

በኢሉአባቦር ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት የዳሪሙ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ 2018 ዓ.ም የበጀት ዘመን በሥሩ ላሉት መሥሪያ ቤቶች ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። 

በዚሁ መሠረት፡-

  1. የጽህፈት መሳሪያዎች
  2. የፅዳት ዕቃዎች
  3. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
  4. የቢሮ ዕቃዎች ወይም ፈርኒቸሮችን
  5. የደንብ ልብሶች
  6.  የተለያዩ ጎማዎች
  7. የተለያዩ ህትመቶች
  8. የተለያዩ የግንባታ እቃዎችን

በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል

  1. ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡-
  2. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ።
  3. የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ።
  4. የሚያቀርቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተመሰከረ ቼክ ወይም ሲፒኦ ከውድድር ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ።
  5. የደንብ ልብስን በተመለከተ ግዢው ጥራትን መሠረት በማድረግ ስለሚገዛ የምትወዳደሩ ነጋዴዎች የሚታቀርቡትን ዕቃ ሳምፕል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. የቫት እና TIN No ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
  7. በህጋዊ መንገድ ስለመደራጀታቸው በአቃቤ ህግ የተመሰከረ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
  8. አሸናፊ ተጫራቾች ለመልካም ሥራ አፈፃፀም የጠቅላላ ዋጋውን 10%ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  9. ተጫራቾች ሰነዱን ሲያስገቡ ስም፣አድራሻ፣ ፈርማ ያለበት እና ኦሪጂናል እና ኮፒ ሰነድ ማምጣት አለበት።
  10. ተጫራቾች ከ አሸነፉ በኋላ ውል ለመፈራረም ፈቃደኛ የሆነ እና እቃውን ሲያስገቡ ጥራቱን የጠበቀ መሆን አለበት።
  11. ተጫራቾች ጋዜጣው ከወጣበት ቀን አንስተው ለተከታታይ 30(ሰላሳ) የሥራ ቀናት የጨረታውን ሰነድ ከኢሉባቦር ዞን ዳሪሙ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በመውሰድ ሁሉንም ሰነድ በአንድ መቶ ብር በመግዛት ዋጋውን ሞልተው ከገዙበት ቀን ጀምሮ እስከ 10/01/2018 ቀን ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። 
  12. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በ10/01/2018 ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  13. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ10/01/2018 ቀን በ 8፡30 ሰዓት በግልፅ ይከፈታል፡፡
  14. የዕቃው ማስረከቢያ ቦታ ዳሪሙ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ሆኖ ጠቅላላ ወጪ የሻጩ ግዴታ ይሆናል።
  15. በሌላ ተጫራቾች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
  16. ስርዝ ድልዝ ያለው ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  17.  የዕቃው ብዛት ከውድድር በኋላ የሚገለፅ ይሆናል።
  18. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።
  19. ከተራ ቁጥር 1-18 በተጠቀሰው ያልተስማማ በመጨረታው መሳተፍ የለበትም ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0911 970 658 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡

በኢሉአባቦር ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት የዳሪሙ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት